ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በስፋት እየተሰራጨ ያለውን በክትባት የተገኘ የፖሊዮ ቫይረስ ዓይነት 2 (cVDPV2) ወረርሽኝ ለመቆጣጠር የምታደርገውን ጥረት እያፋጠነች ባለችበት ወቅት፣ የዓለም ፖሊዮ ቀን 2025 በሮታሪ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ አዘጋጆነት መከበሩ ተገልጿል።
በየዓመቱ ጥቅምት 24 የሚከበረው የዓለም ፖሊዮ ቀን የዘንድሮው መሪ ቃል “ፖሊዮን እናስወግድ፡ እያንዳንዱ ልጅ፣ እያንዳንዱ ክትባት፣ በሁሉም ቦታ” የሚል ሲሆን፣ ይህ የመታሰቢያ ቀን እኤአ ከ1988 ጀምሮ በፖሊዮ ጉዳዮች ላይ የተመዘገበውን 99% ቅነሳ ከማክበር በተጨማሪ፣ የክትባት፣ የማገገሚያ ዕውቀትና ዓለም አቀፍ ጨርሶ የማጥፋት ጥረቶችን የሚያበረታታ ጭምር መሆኑ ተጠቁሟል።
የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የክትባት መከላከያ በሽታዎች የክትትልና ምላሽ ቡድን መሪ የሆኑት ዶ/ር ሚክያስ ዓላዩ በዚሁ ዕለት እንደገለጹት፣ በሀገሪቱ በክትባት የተገኘ ፖሊዮ ቫይረስ ሪፖርት መደረጉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን ከ2019 ጀምሮ ሪፖርት የተደረጉት ጉዳዮች ቁጥር ከፍ ያለ መሆኑን አስምረውበታል።
CapitalNews
