በአሜሪካ በሺዎች የሚቆጠሩ በረራዎች መሠረዛቸው ተነገረ።
ዋና ዋና የአሜሪካ አውሮፕላን ማረፊያዎች በመዘጋታቸው ምክንያት 10 በመቶ በረራዎች
መቋረጣቸውም ተነግሯል።
የአሜሪካ የአየር ትራፊክ ቁጥጥር በአሜሪካ ያሉ ዋና ዋና የአውሮኘላን ጣቢያዎችን መዘጋቱን ተከትሎ ነው በሺዎች የሚቆጠሩ በረራዎ ስተጓጎላቸውና መሰረዛቸው የተነገረው።
ትዕዛዙ ከተላለፈ በኋላ ትላንት አርብ ብቻ ከ2ሺ በላይ የአሜሪካ በረራዎች መስተጓጎላቸውና መሰረዛቸው ተነግሯል።
የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር (ኤፍኤኤ) በመጪው ሳምንት መጨረሻ የአየር መንገድ አገልግሎቱ ወደነበረበት እንደሚመለስ ገልጿል።
በረራቸውን የሰረዙት የአሜሪካ አየር መንገዶች፥ በረራዎቻቸው የተሰረዘባቸውን ደንበኞች ሙሉ ገንዘብ ተመላሽ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።
