ሀገራችን ኢትዮጵያዊ በዓለም መድረክ ላይ በቴኳን-ዶ ስፖርት ስሟ ከፍ ብሎ ተነሳ!!! HALL OF FAME GALL & AWARDS BANQUET NIGHT. November 8 2025 WINNER
ማስተር ኤልያስ ኩመል ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በዓለም አቀፍ የማርሻል አርት ውድድሮች ላይ በመሳተፍ ከ20 በላይ ሜዳልያዎችን ያሳካ ሲሆን በያዝነው ዓመት እ.ኤ.አ November 8 2025 የዓለም አቀፉ Professional Taekwondo Federation በፊሊፒንስዋ ባጉዊ ከተማ አዘጋጅቶት በነበረው በቴኳንዶ ብዙ የሰሩ እና ተፅዕኖ የፈጠሩ በዓለም ዙርያ ላይ ያሉ ታላላቅ ሰዎች በሚሸለሙበት HALL OF FAME GALA & BANQUET NIGHT ላይ በመገኘት በሙያው ላበረከተው ታላቅ አስተዋፅዖና በውድድሩ ላይ ከአፍሪካ በብቸኝነት በመሳተፍና በማሸነፍ የዘርፋን ትልቁን ሽልማት (አዋርድ) ተሸልሟል።በተጨማሪም Professional Taekwondo 6th Dan ባለቤትም መሆን ችሏል።
ማስተር ኤልያስ ከሽልማቱ በኃላም ” ለኔ ቦታው ላይ ተገኝቼ አሸንፌ ከተሰጠኝ ትልቁ ሽልማት ይልቅ የቴኳንዶ ፈጣሪ እና አባት ከሆኑት የቾይ ልጅ ከሆነው ከግራንድ ማስተር ጁንግ ሁዋ እጅ ሽልማቱን በመቀበሌ በእጅጉን ኮርቻለሁ” ሲል ተናግሯል ።
ማስተር ኤልያስ ኩመል ሽልማቱን ካገኘ በኃላ ወደሀገሩ የተመለሰ ሲሆን በርካታ የሞያ አጋሮቹ እና የፌዴሬሽኑ አመራርና አባላት አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በመገኘት አቀባበል አድርገውለታል።።
My sincere thanks to Honorable Grand Master Rick W shin and the Professional TaekwonDo leaders.
