በጾታዊ ጥቃት ወደ ህክምና ከሚሄዱት እስከ 80 በመቶ ከ18 ዓመት በታች ናቸው

Date:

በአዲስ አበባ በጾታዊ ጥቃት የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ከሚሄዱት መካከል ከ70 እስከ 80 በመቶ የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ያሉ ልጆች ናቸው ተብሏል።

በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሴቶች ህጻናት ጉዳይ ዳይሬክተር ሄለን አዱኛን አናግሮ በሰራው ዘገባ  በልጆች ላይ የሚደርሰው ጾታዊ ጥቃት እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሷል።

ቢሮው ጥቃት ደርሶባቸው ህክምና ለማግኘት ከሚመጡት ተገልጋዮች ውስጥ 90 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች 10 በመቶዎቹ ወንዶች መሆናቸውንም ዳሬክተሯ ተናግረዋል።

አክለውም፥ 60 በመቶ የሚሆኑት ጥቃት አድራሾች የተጠቂዎቹ የቅርብ ቤተሰብ ወይም በቅርብ ያሉ ሰዎች መሆናቸውን ጠቅሰው፥ 40 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ የማያውቋቸው ሰዎች እንደሆኑ ነው የገለጹት።

ዘገባው ጥቃት ከደረሰባቸው መካከል በኤች አይ ቪ እና ሌሎች የአባላዛር በሽታዎች የተያዙ ተጠቂዎች ቁጥር አነስተኛ ቢሆንም በበሽታዎቹ መያዛቸው የታወቁ እንዳሉ ጠቅሷል።

አራዳ ኤፍ.ኤም

@TikvahethMagazine

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...