ቢሮው ያለ ረዳት አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎች በከተማዋ እየበዙ ነው ያለ ሲሆን ከዚህ በኋላ በመመሪያው መሰረት ረዳት የሌላቸውን ታክሲዎች እቀጣለሁ ብሏል።
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የትራንስፖርት አገልግሎት ክትትልና ኢንስፔክሽን ዳይሬክተር አቶ ጌትነት ታመነ ያለ ረዳት ማሽከርከር ገንዘብ በመቀበል፣ ገቢና ወራጅ በመቆጣጠር የሹፌሩን ትኩረት ስለሚሰርቅ ለአደጋ ያጋልጣል ብለውናል።
ኃላፊው ከዚህ ቀደም ለሌሎች የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ብቻ ትኩረት በመስጠታችን ረዳት ያላቸውና የሌላቸውን ተሽከርካሬዎች የመለየት ውስንነት ታይቶብናል ብለዋል።
ከዚህ በኋላ ግን የታክሲ ረዳት መኖር አንዱ የትራፊክ ደህንነት አካል በመሆኑ ሁሉም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ላይ ክትትል እናደርጋለን ብለዋል።
