የአፍሪካ ሕገ-መንግስታዊ ፍርድ ቤቶችና መሰል ተቋማት ዓለም አቀፍ ሲምፖዝየም በአዲስ አበባ ይካሄዳል

Date:


የአፍሪካ ሕገ-መንግስታዊ ፍርድ ቤቶችና መሰል ተቋማት ዓለም አቀፍ ሲምፖዝየም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኢፌድሪ ሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አስታወቀ።

አጣሪ ጉባኤው 4ኛውን የአፍሪካ ሕገ-መንግስታዊ ፍርድ ቤቶችና መሰል ተቋማት ዓለም አቀፍ ሲምፖዝየም አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኅን መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የኢፌድሪ የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ደሳለኝ ወዬሳ፤ ሲምፖዝየሙ ህዳር 19 በአፍሪካ ሕብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ መካሄድ ይጀምራል ብለዋል።

በሲፖዝየሙ የአባል ሀገራቱ የሕገ-መንግስታዊ ፍርድ ቤቶች ፕሬዝደንቶች፣ በዓለም አቀፍ ተቋማት የሚሰሩ የዘርፉ ምሁራን እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚታደሙ ተናግረዋል።

የአፍሪካ ሕገ-መንግስታዊ ፍርድ ቤቶችና መሰል ተቋማት ዓለም አቀፍ ሲምፖዝየም “ሕገ-መንግስታዊነትና ሀገረ መንግስት ግንባታ” በሚል መሪሃሳብ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።

በመድረኩ ኢትዮጵያም ከምታጋራው ተሞክሮ በተጨማሪ በዘርፉ ላይ የተደረጉ በርካታ የምርምር ውጤቶች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው አመላክተዋል።

በሲምፖዝየሙ ለመሳተፍም እንግዶች ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ እንደሚገኙ ጠቁመው፤ ተሳታፊዎች በሚኖራቸው ቆይታ በአዲስ አበባ የተለያዩ ስፍራዎችን እንደሚጎበኙ አስረድተዋል።

ሲምፖዝየሙን በተሳካ መንገድ ለማካሄድም አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...

የተጀመሩ የትምህርት ሪፎርሞችን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም በቁርጠኝነት መስራት ይገባል

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ...

የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የቡና ገበያ መዳረሻዎች እየፈለገ ነዉ

በፈረንጆቹ 2023 የፀደቀው የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ህግ ምርቶች...