ባንኩ እንዳስታወቀው ፤ በ 2017 ዓ.ም. በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከግብር በፊት የተገኘው የ2.6 ቢሊዮን ብር ትርፍ፣ ካለፈው ዓመት ከነበረው 1 ቢሊዮን ብር ትርፍ አንፃር የ155% ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል።
ይህ አዕድገት የተገኘው በሂሳብ ዓመቱ ባንኩ 12.36 ቢሊዮን ብር ጠቅላላ ገቢ በማስመዝገብ ከእቅድ በላይ 105% ብልጫ በማሳየቱ እንደሆነ ዛሬ ባካሄደው 16ኛው የባለአክሲዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ አስታውቋል።
እንደ ባንኩ ሪፖርት የዲጂታል አገልግሎቶች ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር በ50% በማደግ 5.7 ሚሊዮን መድረሱንና በተለይም ሚልኪ (Milkii) ዲጂታል ፋይናንሲንግ ፕላትፎርም ተጠቃሚ በመሆን ከ80,000 በላይ ተበዳሪዎች በAI በመታገዝ ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ያለዋስትና ብድር ተጠቃሚ እንደሆኑ አመልክቷል።
