Date:

” እገዳው መሰረተ ቢስና የማይተገበር ነው “– በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ።

ደብረፅዮን (ዶ/ር) የሚመሩት ህወሓት ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ሦስት ከፍተኛ የሰራዊት አመራሮች ላይ የወሰዱት ጊዚያዊ የእግድ እርምጃ አስመልክቶ ሌሊት 8 ሰዓት አካበቢ መግለጫ አውጥቷል።

በዚህም ፕሬዜዳንቱ የወሰዱት እርምጃ ” በሌለ ስልጣናቸው የወሰዱት የማይተገበር ” ሲል በፅኑ ተቃውሞታል።

” እገዳው መሰረተ ቢስና የማይተገበር ” ሲል ውድቅ ያደረገው መግለጫው ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳን ” ከስልጣቸው የኋላፊነት ቦታ ማንሳቱን ” አስታውሰዋል።

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን ” አምባገነን ፕሬዜዳንት ነበር ” ሲልም አጣጥሏቸዋል።

” የእግድ እርምጃውን የተደራጀ ሰራዊት ለማፍረስ ሲደረገው የቆየው ተንኮል አካል ነው ” ያለ ሲሆን ” እርምጃው አደገኛ ውጤት የሚያስከትል ነው ” ሲል አስጠንቅቋል።

” መሰረተ ቢስ ” ሲል የገለፀው የሦስቱ ከፍተኛ የሰራዊት አመራሮች ጊዚያዊ እግድ ፤ የሰራዊት አባላትና ህዝቡ እንዳይቀበሉት የሚል ጥሪም አስተላልፏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...

ኧረ ፋታ ስጡን?!

መንግስት ግን" ምን ሁኑ ?" ሊለን ነው :: አጀንዳ...