
“የእብድ ውሻ በሽታ የህብረተሰብ ጤና ችግር እየሆነ መጥቷል” – የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ባለፉት ሰባት ወራት ከእብድ ውሻ በሽታ ጋር በተገናኘ ከ30 በላይ ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል።
በበሽታው የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍ እያለ መምጣቱ የተገለጸ ሲሆን በየሳምንቱ ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች በእብድ ውሻ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑም ተመላክቷል።
የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የእብድ ውሻ በሽታ የህብረተሰብ ጤና ችግር እየሆነ መጥቷል ሲል ገልጿል ሲል ሀገሬ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
ውሾችን በጊዜ አለማስከተብ እና ህብረተሰቡ ለክትባት ያለው ግንዛቤ አነስተኛ መሆን እንዲሁም በክልሉ ያለው የፀጥታ ሁኔታ ችግሩ እንዲባባስ እና የቅድመ መከላከል ስራዎች እንዳይሰሩ እንቅፋት ሆኗልም ተብሏል።