300ሺ ሰዎች ያለቁበት የዳርፉር የጦር ወንጀል

Date:

ዓለም አቀፉ የጦር የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በዳርፉር የጦር ወንጀል መፈጸሙን ባመነው ቀድሞው የጃንጃይድ ሚሊሻ መሪ ላይ የሃያ ዓመት እስራት ቅጣት አስተላለፈ። በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2003 እና 2004 በጃንጃይድ ሚሊሻ በዳርፉር የተፈጸሙ ተያያዥ ወንጀሎችን በሚመለከት ፍርድ ቤቱ እንዲህ ዓይነት ውሳኔዎችን ሲያሳልፍ ይህ የመጀመሪያው መሆኑም ተገልጿል።

አሊ ኩሺያብ ወይንም በሙሉ ስማቸው አሊ ሙሀመድ አሊ አብድ-አል-ራህማን በመባል የሚታወቁት የጃንጃይድ ሚሊሻ የቀድሞ መሪ በሱዳን ዳርፉር በሰብዓዊነትና በሰው ልጆች ላይ አሰቃቂ ግድያዎችን ጨምሮ የጦር ወንጀል መፈጸማቸውን ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ ማመናቸውን ተከትሎ የሃያ ዓመት እስራት የተላለፈባቸው መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል።

የቀድሞው የጃንጃይድ መሪ አሊ ኩሺያብ በንጹሐን ላይ ጥቃት መፈጸም፣ ግድያ፣አስገድዶ መድፈር፣ ሰዎችን ማሰቃየት፣ ዝርፊያ፣ ንብረት ማውደም፣ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርና በሃይማኖታቸው ወይም በብሔር ማንነታቸው የተነሳ በሰዎች ላይ ጭካኔ የተሞላባቸው ግፎችን መፈጸምን ጨምሮ ብቀረቡባቸው 31 ዓይነት ክሶች በሁሉም ጥፋተኛ ሆነው መገኘታቸውን የዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ገልጿል።

ፍርድ ቤቱ አሊ ኩሺያብ ወይንም በሙሉ ስማቸው አሊ ሙሀመድ አሊ አብድ-አል-ራህማን በመባል የሚታወቁት የቀድሞው የጃንጃይድ መሪ ሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት በነበረችበት ወቅት በዳርፉር በተፈጸመው የጦር ወንጀል መሪ ተዋንያን የነበሩ መሆናቸውን ማረጋገጡንም ብይኑን በሰጠበት ወቅት አስታውቋል።

ይህንንም “መጥረቢያ ጭምርን በመጠቀም ሰዎችን በመደብደብና ለገዳዮች የግድያ ትዕዛዝ በመስጠት አሊ ሙሀመድ አሊ አብድ-አል-ራህማን በግሉ በዳርፉር በተፈጸመው የጦር ወንጀል መሳተፉን አረጋግጠናል” ሲሉ ውሳኔውን ያስተላለፉት ዳኛ ጆሐና ኮርነር ተናግረዋል።

ግለሰቡ በዳርፉሩ የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት ወቅት ሰዎችን በኃይል ከቀያቸው የማፈናቀል፣ ሰብዓዊ ክብር የጎደላቸው ወንጀሎችን በሰዎች ላይ የመፈጸምና የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን መፈጸሙን ተበዳዮችን ጠቅሰው ዳኛ ጆሐና ገልጸዋል።

አሊ ኩሺያብ በበኩሉ በአውሮፓውያኑ 2021 መጀመሪያ በተጀመረው የክስ ሂደት “አሊ ኩሽያብ እኔ አይደለሁም” በማለት ፍርድ ቤቱ በስህተት በእርሱ ላይ ክስ መመስረቱን ጠቅሶ ተከራክሮ የነበረ ቢሆንም ሙግቱ በዳኞች ውድቅ ተደርጓል።

ይሁን እንጂ ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ በተደረገ የፍርድ ሂደት አሊ ኩሺያብ ጥፋቱን መፈጸሙን በማመኑ በዛሬው እለት የሃያ ዓመት እስር ቅጣት ተላልፎበታል።

አቃቢ ሕግ “ሁለት ሰዎችን በመጥረቢያ ቀጥቅጦ የገደለውና ዛሬም በብዙዎች አዕምሮ ውስጥ ያልጠፉት የእነዚያ አረመኔዎች አባልና መሪ የሆነው የጦር ወንጀለኛ በእጃችሁ ላይ ነው ያለው” በሚል በግለሰቡ ላይ የተፈረደው የሃያ ዓመት ክስ የሚያንስ መሆኑን በመግለጽና አሊ ኩሺያብ በዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ፤ የግለሰቡ ጠበቃ በበኩላቸው የሰባት ዓመት የፍርድ አመክሮ እንዲደረግለት ተከራክረው የነበረ ሲሆን ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ሙግት አዳምጦ የሃያ ዓመት እስራት ፈርዶበታል።

በሱዳን በዳርፉር በነበረው የእረስ በእርስ ጦርነት ወቅት ከ300 ሺሕ ሰዎች መገደላቸውንና 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንገስታት ድርጅት መረጃ ያመላክታል።

ይህ ወንጀል በአብዛኛው በአረብ ሚሊሻ ወታደሮች የበላይነት በተያዘውና አሁን በሃያ ዓመት እስራት የተቀጡት አሊ ኩሺያብ ከመሪዎቹ መካከል አንዱ የነበሩበት የጃንጃዊድ ሚሊሻ ሲሆን ጥቃቱ ያነጻጸረውም በዳርፉር አረብ ባልሆኑና በጥቁር አፍሪካዊ ሱዳናውያን ላይ እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ።

ከዚሁ ሚሊሻ እንደተወለደ የሚነገርለት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይልም እንደዚሁ በአሁኑ የሱዳን የእርስ በእረስ ጦርነት በለፈው ወር ዋና ከተማዋን አል-ፋሽር ከተማን ከተቆጣጠረ ወዲህ በዳርፉር በተመሳሳይ የጦር ወንጀሎች መፈጸሙ በስፋት ሲዘገብ የቆየ ጉዳይ መሆኑ ይታወቃል።

(አዲስ ማለዳ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...