የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማኅበር እጩ ጠበቃ መሰረት ስዩም ማን ናቸው?

Date:

ጠበቃ መሰረት በሕግ ማማከር እና ጥብቅና አገልግሎት የደረጀ የረጅም ጊዜ ልምድ ባለቤት ናቸው፡፡ በሀገር አቀፍ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ17 ዓመት በላይ የሙያ አገልግሎት ልምድ እና ተሞክሮ አላቸው፡፡

የትውልድ ቦታቸው፣ ዕድገታቸው እና የሁለተኛ ደረጃቸውን የተከታተሉት ፍቼ ሰላሌ ነው፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪ በህግ (LLB) ያገኙ ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ የንግድ አስተዳደር ደግሞ ሁለተኛ ዲግሪ አግኝተዋል፡፡

ሙያቸውን ለማዳበርም ከሕግ እና ቢዝነስ አስተዳደር ጋር የተያያዙ በርካታ ዓለም ዓቀፍ ሥልጠናዎች ተከታትለው አጠናቅቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፍትህ እና የህግ ጉዳዮች የሪፎርም አማካሪ ጉባኤ አባል በመሆን፤ አማካሪ ጉባኤው የሪፎርም ለውጥ ባደረገባቸው ህጎች ላይ ክለሳ በማድረግ ሂደት ንቁ ተሳትፎ አድርገዋል፡፡

የፀረ ሽብር ህግ አዋጅ 652/2009 ያሻሻለው አዋጅ 1176/2020፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ 621/2009 ያሻሻለው አዋጅ 1113/2019፣ የንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 1243/2021፣ የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ 1183/2020 እና የፌደራል ጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ 1249/2021 በማርቀቅ ሂደት ከተሳትፎ የላቀ አበርክቶ አላቸው፡፡

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የሕግ ተቋም የሆነው ማኩታ የጥብቅና አገልግሎት ድርጅት መሥራች እና ማኔጂንግ ፓርትነር ናቸው፡፡

በዚህ የሕግ ተቋማቸው አማካኝነትም ለበርካታ ባለሙያዎች የሥራ ዕድልን ከመፍጠራቸውም በላይ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስጠብቁ በርካታ ሥራዎችን ሠርተዋል፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ ጉልህ ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ፕሮጀክቶች ላይ የተሰማሩ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎችን በመወከል ለፕሮጀክቱ መሳካት በሕግ ማማከር መስክ ተገቢውን ሙያዊ አበርክቶ አድርገዋል፡፡

አዲሱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት፣ የአደይ አበባ አዲሱ የስታዲየም ግንባታ ፕሮጀክት፣ የወልቃይት የስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክቶች፣ ካሉብ እና ኢላላ ጋዝ ፕሮጀክት፣ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ሕንጻ እና የባህርዳር መንገድ ፕሮጀክት በሙያቸው የማማከር ሥራ የሠሩባቸው ፕሮጀክቶች ናቸው፡፡

ከ100 ሀገር በላይ የተወጣጡ 400 የሕግ ልህቃን ያሉበት የLD Legal Alliance መስራች እና ተሳታፊ ናቸው፡፡ ቱርክ አንካራ በተደረገዉ ‘ኢንተርናሽናል ሎዉ’ ሴሚናር ተሳታፊ የ”Declaration on the Protection of The Extraterritorial Reputation Rights of Heads of State Worldwide and the Legal Rights of Diaspora Residents in Third Countries, Especially Women and Children” የሜይ 2025 (አንካራ የዲክላሬሽን) ፈራሚ ከሆኑ 11 የሕግ ልህቃን ብቸኛ አፍሪካዊት ወኪል የሕግ ባለሙያ ናቸው፡፡

የቅን ኢትዮጵያ ማኅበር የቦርድ ሰብሳቢ፣ ጆሽዋ ዩዝ አካዳሚ ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ፣ የዓድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ የቦርድ አባል፣ ዓለም አቀፍ የሽምግልና እና የግልግል ማዕከል አደራጅ እና መሥራች አባል፣ የኪን ሪል እስቴት የቦርድ ምክትል ሊቀመንበር፣ ዓለም አቀፍ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር (IBA) ውስጥ ሰፊ ልምዳቸውን አጋርተዋል፡፡

እንደ ቴንጃን ፍርድ ቤት፣ ICC ፍርድ ቤት፣ as DRB members case base፣ As DB member case base ያሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥም ንቁ ተሳትፎ አላቸው፡፡

የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይም ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ በFiker Integrity NGO በኩል ከ15 ተማሪዎች በላይ ሙሉ የትምህርት ወጪ በመሸፈን እያስተማሩ ሲሆን፣ ለቻንኮ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መሣሪያ እንዲሟላ አድርገዋል፡፡

የፌደራል ፍ/ቤቶች ምቹ የችሎት ማስቻያ ስፍራ እንዲኖራቸው የቢሮ እድሳት እና የቢሮ አገልግሎት ቁሳቁስ ለፌ/የመ/ደ/ፍ/ቤት የድጋፍ ማስተባበር ሥራ በብቃት በመሪነት አከናውነዋል፡፡
የፌደራል ፍ/ቤት ሠራተኞች ምቹ የህፃናት ማቆያ እንዲኖራቸው የፋይናስ እና የቁስ ድጋፍ በማሰባሰብ ተደራጅቶ አገልግሎት እንዲሰጥ በማድረግ ረገድ አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡

የአፍሪካ ጠበቆች ማኅበራት ህብረት (PALU) ጉባኤ በአዲስ አበባ በስኬት እንዲከናወን እና የጠበቃው ማኅበረሰብ ጠንካራ ትስስሮች እንዲፈጠርለት ፕሮግራም በማሳናዳት እና ማስተባበር ሚና ተወጥተዋል፡፡

GMM TV ዘወትር ቅዳሜ ህግ ምን ይላል የተሰኘ የማኅበረሰቡን የሕግ ንቃተ ህሊና የሚያሳድግ ፕሮግራም በማዘጋጀት እና በመምራት የላቀ ማኅበራዊ አበርክቶ አድርገዋል፡፡

ጠበቃ መሰረት የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማኅበር ፕሬዚዳንት ሆነው ቢመረጡ ምን ሊሠሩ አስበዋል?

ከላይ በጥቂቱ የተጠቀሱትን ሰፊ ልምድ ያላቸው ጠበቃ መሰረት ስዩም ታኅሳስ 04 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚደረገው የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማኅበር ፕሬዚዳንትነት ይወዳደራሉ፡፡ የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ሆነው ቢመረጡ የአባላቱን መብት ማስከበር፣ የአባላቱን አቅም ማጎልበት፣ አባላት የተሻለ ገቢ የሚያገኙበትን መንገድ ማመቻቸት እና ጠበቆች የፍትህ ሥርዓቱ ውስጥ ያላቸው ሚና የላቀ እንዲሆን እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል፡፡

ጠበቃ መሰረት ለዚህ ኃላፊትነት ድምፃችሁን ብትሰጡአቸው አደራችሁን አክብረው በትጋት ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...