ከ40 በላይ የሰሃራ በታች አፍሪካ ሀገራትን በባቡር ለማገናኘት ያለመ ፕሮጀክት

Date:


ኢትዮጵያ እና የናጀሪያው ኢንሳይት ዳይናሚክስ ሪሶርስስ Gas-by-Rail Economic Corridor Initiative ለማሳደግ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።


የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና ኢንሳይት ዳይናሚክስ ሪሶርስስ Gas-by-Rail Economic Corridor Initiative ለማሳደግ የመግባቢያ ስምምነት (MoU) በይፋ ተፈራርመዋል፣


በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሁለገብ አዳራሽ የተካሄደው የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን፣ ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከአጋር ተቋማት የተውጣጡ ተወካዮችን እና ባለድርሻ አካላትን አሰባስቧል።


በኢትዮጵያ በኩል የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ባሬኦ ሃሰን እና የኢንሳይት ዳይናሚክስ ሪሶርስን ወክለው ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ ሙሳ ኢብራሂም ኩቺ ስምምነቱን ፈርመዋል።
ክቡር አቶ በረኦ ሀሰን ስምምነቱ ከኢትዮጵያ አረንጓዴ ትራንስፖርትን የማስፋፋት አገራዊ አጀንዳ ጋር የሚጣጣም መሆኑን ገልጸዋል ።


ስምምነቱ በነዳጅ ምትክ የታዳሽ ኃይል እና የተፈጥሮ ጋዝ አጠቃቀምን በማበረታታት፣ ፕሮጀክቱ ለአየር ንብረት ቅነሳ ጥረቶች አስተዋጽኦ የሚያደርግ ሲሆን ከ40 በላይ ከሰሃራ በታች ባሉ ሀገራት በባቡር ትራንስፖርት በማገናኘት አህጉራዊ ውህደትን ያሻሽላል ተብሎ ይጠበቃል።


በቀጣይ ወራት በአዲስ አበባ ከመላው አፍሪካ ከ 1000 በላይ ተሳታፊዎችን ያካተተ የንግድ ጉባኤ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ለማካሄድ ተግባብተው ስምምነት ተፈራርመዋል ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...