የኦሮሚያ ክልል የመጀመሪያ ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት አቶ ሀሰን አሊ ከ29 ዓመታት ቆይታ በኋላ በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
አቶ ሀሰን አሊ ከቤተሰቦቻቸው ጋር አዲስ አበባ ሲገቡ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዚህ ወቅት÷አቶ ሀሰን አሊ ከሶስት አስርት ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ሀገራቸው ሲገቡ አቀባበል ስላደረጉላቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡
አቶ ሀሰን አሊ በኦሮሞ ሕዝብ ትግል ውስጥ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱና ክልሉ አሁን ለደረሰበት ደረጃ ሚናቸው ጉልህ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡
