ከጥር 3 እሰከ ጥር 12 ቀናት ከሳይቤሪያ ከፍተኛ የአየር ግፊት ላይ በመነሳት ወደ ሀገራችን የሚነፍሰው ደረቅ እና ቀዝቃዛ አየር እንደሚኖረው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘም የበጋው ደረቅ፣ ፀሐያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛዎቹ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የሚስተዋል ሲሆን፤ የሌሊትና የማለዳዉ ቅዝቃዜ በተለይም በሰሜን፣ ምስራቅ፣ መከከለኛዉና ደቡብ ደጋማ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ቀጣይነት ይኖረዋል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በመካከለኛዉ፣ ምሥራቅ፣ በመካከለኛዉ እና የደቡብ ደጋማ ቦታዎች ላይ የለሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ ከአምስት (5) ዲግሪ ሴልሺየስ በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ።
በሌላ በኩል በጸሀይ ኃይል ታግዘው የሚፈጠሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ጋር ተያይዞ በመጨረሻዎቹ ቀናቶች ላይ የተሻለ ጥንካሬ ይኖራቸዋል፡፡
ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብ አሮሚያ ዞኖች፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡባዊ ዞኖች እና ጥቂት የደቡብ ሶማሌ ዞኖች ላይ አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
በተጨማሪም በሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት አልፎ አልፎ በሚኖሩት ቀናት ወቅቱን ያልጠበቀ አነስተኛ መጠን ያለዉ ዝናብ እንደሚኖር የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት
