ጤፍ እንጀራ ብቻ መሆኑ ቀርቶ ወተትም ሆኖ የአለምን ገበያ ተቀላቅሏል

Date:

በአለም የመጀመሪያ የሆነ የጤፍ ወተት በኢትዮጵያዊ ድርጅት በእንግሊዝ ሀገር ተመዝግቦ ገበያውን ተቀላቅሏል፡፡

ኦሪጅናል ቴፍሊ በተባለው ተቋም ቴፍሊ የሚል መጠሪያን ይዞ ወደ ገበያው የገባው የጤፍ ወተት ልክ እንደ አልመንድ እና አኩሪ አተር ወተት ሁሉ ከእፅዋት የተሰራ የወተት ምርት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በለንደን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተሰናዳ ዝግጅት የጤፍ ወተት በአለም የመጀመሪያ ምርት ሆኖ መመዝገቡ ይፋ ተደርጓል፡፡

አቶ ዮሴፍ ብርሃኔ ኑሮአቸው በእንግሊዝ ሀገር ሲሆን ከጤፍ የተሰራ ወተትን አምራች ኩባንያው መስራችና ዋና ዳይሬክተር ናቸው፡፡

አቶ ዮሴፍ ከእፅዋት ምርት የሚገኝ ወተት በአለም ዙሪያ እያደገ የመጣና ትልቅ ገንዘብ የሚገላበጥበት ኢንዱስትሪ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በእንግሊዝ ሀገር ብቻ በ5 ዓመት ጊዜ ውስጥ 1.3 ቢሊዮን ዶላር የሚገላበጥበት፤በአለም ዙሪያም በዚሁ ኢንዱስትሪው የሚኖረው አቅምከ75 እስከ 100 ቢሊዮን ዶላር የሚሆንበት ትልቅ ቢዝነስ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ጤፍም ወተት በመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ከዕፅዋት የሚገኝ የወተት ምርት ዝርዝር ውስጥ ገብቷል፡፡

ጅርጅቱ ምርቱን ከኢትዮጵያ ገበሬዎች ጤፍን በመውሰድ በእንግሊዝ ሀገር ባለው ፋብሪካ እያመረተ መሆኑ ተነግራል፡፡

ወደፊት ግን በኢትዮጵያ ፋብሪካን በመትከል የተለያዩ ሌሎች ምርቶችንም በመጨመር የገልፍ ሀገራትና የአፍሪካን ገበያ የመቆጣጠር ፍላጎት እንዳላቸው አቶ ዮሴፍ ተናግረዋል፡፡

በቅርብ ጊዜ ውስጥም የኢትዮጵያ ቡናን ከጤፍ ወተት ጋር በመቀላቀል የተገኘ ሌላ ምርት (ላቴ) ይዘው ወደ ገበያው እንደሚገቡም ተናግረዋል፡፡

ከዚህኛው ስራ ጎን ለጎን ጤፍ የኢትዮጵያ ሀብታና ቅርስ ጭምር ስለሆነ በአለም የጤፍ ባለቤት ሀገር ኢትዮጵያ መሆኗን ለማረጋገጥ ብዙ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ነግረውናል፡፡

ከመንግስት ጀምሮ በሀገር ውስጥ በአውሮፓና አሜሪካ ያሉ የህግ ሰዎች ሁሉ ተሰብስበው ይህንኑ ሂደት ለማሳካት በጋራ መስራት እንደሚገባቸውም አስረድተዋል፡፡

ቴፍሊ የሚል መጠሪያ የተሰጠው በአለም የመጀመሪያው የጤፍ ወተት በእንግሊዝና በሌሎችም የአውሮፓ ሀገሮች ገበያ መግባት የጀመረ ሲሆን በቅርብ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ገበያም ይመጣል ብለዋል፡፡

ቴዎድሮስ ወርቁ

https://surl.li/ufquyv

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...

አዲስ አበባ፦ የዜጎች ቀይ መስመር!

(የግል አስተያየት) አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን መናገሻ፣ የበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች ለዘመናት...

አብን የምክክሩን ውጤት ውድቅ አደረገ!

አብን በሀገራዊ ምክክሩ ማጠቃለያ ላይ የተፈጸመውን “ሕገ-ወጥ ጣልቃ-ገብነት” በመቃወም...