የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል ሀገራት ወታደሮች እና የጦር መርከቦች ግሪንላንድ መድረሳቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።
ከጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ኖርዌይ፣ ፊንላንድ፣ ብሪታንያ እና ኔዘርላንድስ የተውጣጡ የተወሰኑ ወታደሮች ግሪንላንድ መድረሳቸው ታውቋል።
ከሀገራቱ የተውጣጡ የተወሰኑ ወታደሮች እና ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች በአካባቢው “ቅኝት ለማድረግ” ወደ ስፍራው ማቅናታቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአርክቲክ ደሴቷን “ለደህንነታችን እንፈልጋታለን” ማለታቸው ይታወሳል።
ትራምፕ በከፊል ራስ ገዝ ሆና ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮቿን በዴንማርክ በኩል የምትከውነውን ደሴት ዴንማርክ፥ ከሩሲያም ሆነ ከቻይና አታስጥላትም በሚል ምክንያት ለመያዝ ማሰባቸውን ይናገራሉ።
ይሁን እንጅ ግሪንላንድም ሆነች ዴንማርክ ይህን የትራምፕ ሃሳብ ውድቅ ሲያደርጉ፥ “የአሜሪካ እጅ ረዝሟል” ያሉት የኔቶ አባል ሀገራት ደግሞ ዛሬም ይህ ይህ ቃል ኪዳን መኖሩን “በተግባር ለማሳየት” በደሴቷ መሰባሰባቸውን የፈረንሳዩ ከፍተኛ ዲፕሎማት ኦሊቪየ ፖቭረ ተናግረዋል።
