ከ15,000 በላይ ኢትዮጵያዊያን ህፃናት በጅቡቲ ጎዳናዎች ይገኛሉ

Date:

ህፃናቱ ከሀገር የወጡት በህገወጥ መንገድ ነው ተብሏል፡፡

ይህንን የሰማነው ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው፡፡

ሚኒስቴሩ በህገወጥ መንገድ ከኢትዮጵያ ወጥተው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገር በመመለሱ የተቻለኝ ሁሉ እያደረግሁ ነው ብሏል፡፡

ለዚህም ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት እና ከሚመለከታቸው ጋር እየሰራሁ ነው ሲል ተናግሯል፡፡

በጅቡቲ ባለው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በኩል ህፃናቱ በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ መረጃ ይሰበሰባልም ተብሏል፡፡

በተለያየ ጊዜ ከሀገር የወጡ የበዙ ህፃናትም በድንበር ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ሲሰራ እንደቆየም ተነግሯል፡፡

ይህንን የነገሩን በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህገወጥ ሰዎች ዝውውር መከላከል እና የተመላሽ ዜጎች ጉዳይ መሪ ስራ አስፈጻሚ ደረጄ ተግይበሉ ናቸው፡፡

ከጅቡቲ በተጨማሪ በየመንም በርካታ ኢትዮጵያዊያን ህፃናት እንደሚገኙ ሀላፊው አስረድተዋል፡፡

እነዚህ ህፃናት ፆታዊ እና የተለያዩ ጥቃቶች እንደሚፈጸምባቸውም አንስተዋል፡፡

ህገወጥ አዘዋዋሪዎች ህፃናቱን ለአሸባሪነትና ለውትድርና ጭምርም እንደሚመለምሏቸው አቶ ደረጃ ጠቅሰዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ከህፃናቱ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎቻቸውን እንደሚወሰድም ተነግሯል፡፡

ምስራቅ እና ምዕራብ ሀረርጌ እንዲሁም አፋር አካባቢዎች ህፃናቱ ከሚወጡባቸው ድንበሮች መካከል የተቀጠቀሱ ቦታዎች ናቸው፡፡

ህፃናቱ ድንበር ሲያቋርጡ ወዴት እና ለምን እንደሚሄዱ  ራሱ በቅጡ የማያውቁበት አጋጣሚዎች አሉ ብለዋል፡፡

ወደ ሀገር የተመለሱትም ከቤተሰቦቻቸው የማገኛኘት ስራ እንሰሚሰራም ተናግረዋል አቶ ደረጄ፡፡

ቤተሰቦቻቸው ያልተገኙ እንደሆነ ደግሞ በመጠሊያ ጣቢያዎች ማቆየት፣ በአደራ ቤተሰብ፣ በጉዲፈቻ እና በመሰል አማራጮች ኑሯቸውን እንዲቀጥሉ ይደረጋሉ ሲሉ ሀላፊው አስረድተዋል፡፡

በኢመደበኛ መልኩ ከሀገር መውጣት የበዙ ችግሮች እንዳሉት ተናግሯል የሴቶችና ማህራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፡፡

ህብረተሰቡ ይህንን አውቆ ኢመደበኛ ፍልሰትን በመከላሉ በጋራ እንዲተባበር አሳስቧል፡፡

ሸገር 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...

አዲስ አበባ፦ የዜጎች ቀይ መስመር!

(የግል አስተያየት) አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን መናገሻ፣ የበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች ለዘመናት...

አብን የምክክሩን ውጤት ውድቅ አደረገ!

አብን በሀገራዊ ምክክሩ ማጠቃለያ ላይ የተፈጸመውን “ሕገ-ወጥ ጣልቃ-ገብነት” በመቃወም...