የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ‘የሲስተሙን’ ደህንነት የሚያጠናክር ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት እየተገነባ ነዉ

Date:

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እያደገ የመጣውን የዲጂታል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች ቁጥር ታሳቢ በማድረግ፣ የአገልግሎት መቆራረጥን የሚቀንስና የሲስተም ደኅንነቱን የሚያጠናክር ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት እየገነባ መሆኑን አስታውቋል።

በባንኩ የቴክኖሎጂ ኤክስኪዩቲቭ ፕሬዚዳንት አቶ አማረ አሰፋ “ማንኛውም የቴክኖሎጂ ሥርዓት መቶ በመቶ ከብልሽት ነፃ ማድገረግ ባይቻልም አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የችግሮቹን ስርጭትና የሚወስዱትን የጥገና ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ይቻላል” ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ለዚህም ሲባል ባንኩ ድንገተኛ የቴክኒክ እና የሲስተም ችግሮች ወይም የሳይበር ጥቃቶች አገልግሎቱን እንዳያስተጓጉሉ “ንቁ ዝግጁነት” (Active-Active Standby) የተሰኘ ዘመናዊ የዲዛስተር ሪከቨሪ አሠራር ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል።

ይህ ቴክኖሎጂ አንዱ የሲስተም ክፍል ብልሽት ሲያጋጥመው ወዲያውኑ ወደ ሌላኛው በመቀየር አገልግሎቱ ሳይቋረጥ እንዲቀጥል የሚያስችል የቴክኖሎጂ ጥብቅና ነው። አቶ አማረ አሰፋ አክለውም፣ ባንኩ በሥርዓት ማሻሻያና ጥገና ወቅት የሚያጋጥሙ የአገልግሎት መቋረጦችን አስቀድሞ ለደንበኞች የማሳወቅ ልምዱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

የአገልግሎት ማሻሻያ በሚደረግበት ወቅት ሲስተምን አቁሞ መሥራት ዓለም አቀፋዊ አሠራር መሆኑን የጠቀሱት ፕሬዚዳንቱ፣ ደንበኞች አስቀድመው እንዲዘጋጁ በመገናኛ ብዙኃን መረጃ የማድረስ ሥራ እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል።

ባንኩ ከቴክኖሎጂ ግንባታው ጎን ለጎን የሰው ኃይል ብቃትን የማሳደግ ሥራን እንደ አንዱ ቁልፍ ተግባር ይዞ እየሠራ ይገኛል። ችግሮች ሲፈጠሩ በፍጥነት ለመለየትና መፍትሔ ለመስጠት የባለሙያዎችን አቅም ማጠናከር የሞባይል ባንኪንግና ሌሎች ዲጂታል አገልግሎቶች ቀልጣፋ እንዲሆኑ አስችሏል።

ይህ የባንኩ ጥረት ለሀገሪቱ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ የላቀ ሚና እንደሚኖረው የታመነ ሲሆን፣ ደንበኞችም በሚደረጉ የቴክኖሎጂ ሽግግሮች ላይ ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል። በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ላይ የወጡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት፣ የዲጂታል መሠረተ ልማት ደኅንነትና አስተማማኝነት ለፋይናንስ ተቋማት ተወዳዳሪነት ወሳኝ መሠረት ነው።

(አሐዱ ራድዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...