የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ከ2 ትሪሊዮን ብር በላይ ዓመታዊ ገቢ ማስመዝገቡን አስታወቀ

Date:

ባለፉት ጥቂት ዓመታት በተከናወኑ ጥልቅ የሪፎርም ስራዎች፣ በአንድ ጥላ ስር የሚገኙ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ውጤታማነታቸው በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ብሩክ ታዬ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-

የገቢ ዕድገት፦ የተቋማቱ አጠቃላይ ዓመታዊ ገቢ ከ704 ቢሊዮን ብር ወደ 2.1 ትሪሊዮን ብር አድጓል።

የታክስ ድርሻ፦ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ለሀገሪቱ የታክስ ገቢ ያላቸው ድርሻ 40 በመቶ ደርሷል።

ውጤታማነት፦ ቀደም ሲል በኪሳራ ውስጥ የነበረው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማሻሻያ ስራ ከተሰራበት በኋላ የ2.1 ቢሊዮን ብር ትርፍ አግኝቷል።

ግዙፍ ፕሮጀክቶች፦ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የወርቅ ማጣሪያ እና የክትባት ማምረቻን ጨምሮ 16 ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በማከናወን ላይ ይገኛል።

በአፍሪካ ግዙፉ የሉዓላዊ ሀብት ፈንድ የሆነው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ፤ እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ኢትዮ ቴሌኮም እና ንግድ ባንክ ያሉ ተቋማትን በማስተዳደር የሀገራችንን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እያረጋገጠ ይገኛል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...