የግል ድርጅቶች ጡረታ ፈንድ ወደ ካፒታል ገበያ ሊገባ

Date:

የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የጡረታ ፈንድ ኢንቨስትመንቱን ለማሳደግና አማራጮቹን ለማስፋት ወደ አዲሱ የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ለመግባት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ለፓርላማ አስታወቀ።


የአስተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ አባተ ምትኩ እንደገለጹት፣ ተቋሙ ከሦስት ዓመት በፊት በተደረገ የአዋጅ ማሻሻያ መሠረት ከግምጃ ቤት ሰነድና ከመንግሥት ቦንድ ውጭ በሌሎች ዘርፎች ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ቢፈቀድለትም፣ በአዲስ አበባ የታቀደው የሪል ስቴት ኢንቨስትመንት በመሬት አቅርቦት እጥረት ምክንያት በመጓተቱ ትኩረቱን ወደ ካፒታል ገበያው አዙሯል።


አስተዳደሩ ባለፈው በጀት ዓመት 183 ቢሊዮን ብር ኢንቨስት በማድረግ 14 ቢሊዮን ብር ትርፍ ያስመዘገበ ሲሆን፣ ባለፉት ስድስት ወራት ደግሞ 25.8 ቢሊዮን ብር ገቢና 10.8 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን ጠቁሟል።
ሆኖም በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት የታቀደውን ያህል የጡረታ መዋጮ መሰብሰብና ውዝፍ ክፍያዎችን ማስመለስ ፈታኝ እንደሆነበት የተገለጸ ሲሆን፣ በያዝነው በጀት ዓመት 55 ቢሊዮን ብር መዋጮ ለመሰብሰብና 20 ቢሊዮን ብር የኢንቨስትመንት ትርፍ ለማግኘት አቅዶ እየሠራ ይገኛል።@SECO

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...