ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ በበርሊን ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል ተሸለሙ

Date:

ኃይሌ ገሪማ በጀርመን መዲና በርሊን ትናንት ማክሰኞ በተካሄደ ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል (Berlinale) ላይ ለፊልም ጥበብ ዕድገት የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለሙያዎች የሚሰጠው «የበርሊን ካሜራ» (Berlinale Camera) የክብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ኃይሌ ገሪማ በአፍሪካ ታሪክ፣ በቅኝ አገዛዝ፣ በማንነት እና በማኅበራዊ ፍትህ ላይ በሚያተኩሩ ሥራዎቻቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ ዳይሬክተር፣ አዘጋጅ እና መምህር ናቸው።

ለበርካታ አስርት ዓመታት በአሜሪካ በሚገኘው ሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ  የፊልም ፕሮፌሰር በመሆን በርካታ ወጣት የፊልም ባለሙያዎችን ማፍራታቸው የሚነገርላቸው ኃይሌ ገሪማ በተለይም በአፍሪካ እና በተቀረው ዓለም የሚኖሩ ጥቁር ሕዝቦችን ታሪካዊና ፖለቲካዊ ተሞክሮዎች የሚዘክሩ «ሰንኮፋ» እና «ጤዛ»  በተሰኙ ፊልሞቻቸው አድናቆት አትርፈዋል።

በርሊን ከተማ ውስጥ በሚገኘው  ዴልፊ ፊልም ፓላስት  በተካሄደ ልዩ የፊልም ማሳያ መርኃ ግብር ላይ ፕሮፌሰር ኃይሌ  «ጥቁር አንበሶች ፤ የሮማ ተኩላዎች» (Black Lions – Roman Wolves) የተሰኘውን አዲሱን የፊልም ፕሮጀክታቸውን አስተዋውቀዋል።

አዲሱ የፊልም ሥራቸው ጣሊያን ቅኝ ለመግዛት ያደረገችው ሙከራ በኢትዮጵያ ላይ ያስከተለውን ተጽዕኖ፣ ሙከራውን ለማክሸፍ  የተደረገውን ተጋድሎ እና የታሪክ ትውስታን የሚዳስስ እንደሆነ ተገልጿል።

ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ ዓለም አቀፍ ክብር ያጎናጸፋቸው ሽልማት የተበረከተላቸው ለነጻ የሲኒማ ጥበብ ላላቸው የዕድሜ ልክ ቁርጠኝነት፣ ታሪክን በፊልም የመተረክ ብቃታቸው፣ እንዲሁም የአፍሪካውያንን ድምጽ በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ እንዲሰማ ስላደረጉት ከፍተኛ ጥረት እውቅና ለመስጠት ነው ተብሏል።

ሽልማቱ ፕሮፌሰር ኃይሌ ከተጎናጸፉት ክብር ባሻገር ለኢትዮጵያ እና ለመላው አፍሪካ የፊልም ኢንዱስትሪ ትልቅ ኩራት የሚሆን ነው። በተጨማሪም ዓለምን የሚያስተምር እና የሚያነቃቃውን የኃይሌ ገሪማን የጥበብ ጉዞ በድምቀት የዘከረ ሆኗል።

DW Amharic

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...