በትግራይ  ከ2 ሺ ሄክታር በላይ መሬት በዛፍ አንበጣ ተወረረ

Date:

2ሺህ4መቶ93 ሄክታር መሬት ላይ የዛፍ አንበጣ መከሰቱን ሰምተናል።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት በትግራይ ክልል ግብርና ቢሮ ባለሙያ የሆኑት አቶ አበራ ሀጎስ፤ ከየካቲት 12 ጀምሮ በሰሜን ምዕራብ ዞን የዛፍ አንበጣ መከሰቱን ተናግረዋል፡፡

የዛፍ አንበጣው መነሻው በኤርትራ ድንበር እንደሆነ የገለፁት  ባለሙያዉ፤ አሁን ላይ በዋናነት ያጠቃው ሰብሎችን፣ የእንስሳቱን የግጦሽ ሳር እና የዛፍ አይነቶችን እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

የአንበጣ ዝርያ ተንቀሳቃሽ እንዳልሆነና ከዚህ በፊትም ተከስቶ እንደነበረ ያነሱት አቶ አበራ፤ በአንድ ዛፍ ላይ ወይም በአንድ አካባቢ ብዙ ጊዜ የመቆየት እድል ስላለው የርብርብ ስራ መሠራት እንዳለበት አንስተዋል፡፡

1 ሺ ሁለት መቶ ሄክታር መሬት መከላከል መቻሉንም ነው የገለፁት።

የግብርና ሚኒስቴር አንድ መድኃኒት መርጫ መኪና መላኩን አንስተው ፤በቂ አይደለም የፌደራል መንግስት አስፈላጊዉን ተጨማሪ እርዳታ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።

Ethio fm 107.8

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...

ኧረ ፋታ ስጡን?!

መንግስት ግን" ምን ሁኑ ?" ሊለን ነው :: አጀንዳ...