አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ በፈጸሙት ጥቃት የተገደሉት የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ሚስት መገደላቸውን የአገሪቱ መንግሥት ቴሌቪዥን አረጋገጠ።
የጠቅላይ መሪው ሚስት ማንሱሬህ ኾጃስቴ ባግሄርዛዴህ የተገደሉት “ቤታቸው ውስጥ” መሆኑን ቴሌቪዥን ጣቢያው ገልጿል። ቀደም ሲል የኢራን መገናኛ ብዙኃን ግለሰቧ “ኮማ” ውስጥ እንደነበሩ ዘግበው ነበር።
ቅዳሜ ዕለት በተፈጸመው ጥቃት ከአያቶላህ ኻሜኒ በተጨማሪ ሴት ልጃቸው፣ የልጃቸው ባል እና የልጃቸው ልጅ መገደላቸው ተዘግቧል።
የጠቅላይ መሪው ሚስት ከአያቶላህ ኻሜኒ አራት ወንዶች እና ሁለት ሴት ልጆች ነበሯቸው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የእስራኤል ጦር እሑድ በሊባኖስ፣ ቤይሩት ውስጥ በፈጸመው ጥቃት የሔዝቦላህን የደኅንነት ኃላፊ መግደሉን አስታውቋል።
የእስራኤል ጦር ኃይል “እሑድ ምሽት ቤይሩት ውስጥ በተፈጸመ የተነጣጠረ ጥቃት፣ የሔዝቦላህ የደኅንነት ተቋም አዛዥ የሆነውን ሽብርተኛው ሑሴን ማክሌድን መደምሰሱን አረጋግጧል” ሲል ባወጣው መግለጫ ላይ አስፍሯል።
