የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዜጎቹ በመካከለኛው ምሥራቅ ከሚገኙ 14 አገራት በአስቸኳይ ለቅቀው እንዲወጡ አዘዘ።
የአገሪቱ የቆንስላ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስቴር የሆኑት ሞራ ናምዳር በመሥሪያ ቤታቸው የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ ባሰፈሩት መልዕክት አሜሪካውያን “ሊያጋጥሙ በሚችሉ ከባድ አደጋዎች ምክንያት” ከአስራ አራቱ አገራት “ያሉ የትራንስፖርት አመራጮችን በመጠቀም አሁኑኑ” ለቅቀው እንዲወጡ አሳስበዋል።
የአሜሪካ ዜጎች በአስቸኳይ ለቅቀው እንዲወጡ የታዘዙባቸው አገራት ባህሬን፣ ግብፅ፣ ኢራን፣ ኢራቅ፣ እስራኤል፣ የፍልስጤም ግዛቶች፣ ዮርዳኖስ፣ ኩዌት፣ ሊባኖስ፣ ኦማን፣ ኳታር፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ሶሪያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና የመን ይገኙባቸዋል።
በኩዌት የሚገኘው ኤምባሲ ለየትኛውም የቆስንስላ ጉዳዮች የሚሰጠውን አገልግሎት ማቋረጡን ማስታወቁ ይታወሳል።
