አራተኛ ቀኑን በያዘው አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት ዐበይት ክስተቶች

Date:

አራተኛ ቀኑን የያዘው በአሜሪካ እና በእስራኤል ጥቃት የተጀመረው የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት በርካታ የአካበቢውን አገራት ለኢራን ጥቃት አጋልጦ ቀጥሏል።

  • ዛሬ ማክሰኞ ከማለዳ ጀምሮ እስራኤል በቴህራን እና ቤይሩት “ወታደራዊ ዒላማዎች” ባለቻቸው ስፍራዎች ላይ “ተከታታይ የአየር ጥቃቶች” እየፈጸመች መሆኑን አስታውቃለች።
  • የሳዑዲ መከላከያ ሚኒስቴር በሪያድ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ በሁለት ድሮኖች ጥቃት መፈጸሙን እና መጠነኛ ጉዳት መድረሱን ገልጿል።
  • የኢራን መንግሥት መገናኛ ብዙኃን በባህሬን በሚገኘው የአሜሪካ አየር ኃይል ማዘዣ እና የሠራተኞች ሕንጻ ላይ ጥቃት መድረሱን ዘግበዋል።
  • የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማርኮ ሩቢዮ የአገሪቱ ጦር በኢራን ላይ የሚፈጽመው “ከባዱ ጥቃት ገና እየመጣ ነው” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
  • ጦርነቱ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ ስድስት የአሜሪካ ወታደሮች ተገድለዋል።
  • በኩዌት የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በቀጠናው የተፈጠረን ውጥረት በመጥቀስ ዝግ መሆኑን አስታውቋል።
  • እስራኤል ወደ ሊባኖስ እግረኛ ጦሯን በማስገባት “ተጨማሪ ቁልፍ ስፍራዎችን” ልትቆጣጣር መሆኑን አስታውቃለች።
  • የዩኬው ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪር ስታርመር መንግሥታቸው ጥቃትን ተከትሎ በኢራን በሚመጣ የመንግሥት ለውጥ እንደማያምን ተናግረዋል። ዶናልድ ትራምፕ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተባባሪ አይደሉም ሲሉ ከስሰዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...