“በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ” ዓለም አቀፍ ፎረም  ሊካሄድ ነው

Date:


‎ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ያላትን ዝግጁነት ለዓለም የምታበስርበት 4ኛው “በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ” ዓለም አቀፍ ፎረም በመጋቢት ወር አጋማሽ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው።

‎የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከገንዘብ ሚኒስቴርና ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር መጋቢት 17 እና 18 ቀን 2018 ዓ.ም በሚያካሂደው በዚህ ታላቅ መድረክ ላይ፣ ከ800 በላይ ዓለም አቀፍ ባለሀብቶች፣ የንግድ መሪዎችና ፖሊሲ አውጪዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

‎ኮሚሽነር ዶክተር ዘለቀ ተመስገን እንደገለጸው በባለፈው 3ኛው ፎረም በማዕድንና በሶላር ኢነርጂ ዘርፍ የተሰማሩ አምስት ድርጅቶች በ1.6 ቢሊየን ዶላር ስምምነት ተፈራርመው በአሁኑ ወቅት ሙሉ ለሙሉ ወደ ሥራ የገቡ ሲሆን፤ በዘንድሮው 4ኛው ፎረም ደግሞ ከ2.6 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ የሚያወጡ አዳዲስ የኢንቨስትመንት ስምምነቶች እንዲፈረሙ እቅድ ተይዟል።

‎ይህ ፎረም የንግድ ለንግድ ትስስርን ከመፍጠር ባለፈ፣ ኢትዮጵያ ለውጭ ኢንቨስትመንት ያላትን ምቹ የፖሊሲ ከባቢና የልማት ዕድሎች ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በተግባር የምታሳይበት ወሳኝ መድረክ እንደሚሆን ይታመናል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...