በሚቀጥሉት ቀናት የአየር ንብረት ለውጥ እንደሚኖር ተገለፀ

Date:



‎በሚቀጥሉት አስር ቀናት አዲስ አበባን ጨምሮ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍሎች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር የኢትዮጵያ ሚቴዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል ።

‎አሁን ያለንበትን የየካቲት ወር ጨምሮ እስከ ግንቦት ድረስ በሚዘልቀው የበልግ ወቅት፣ ሰሞኑን እየታየ ያለው የአየር ሁኔታ ለውጥ የሚጠበቅ መሆኑን በማስታወስ ፣ ‎በተለይም የሀገሪቱ ደቡባዊ አጋማሽ ማለትም የሶማሌ ክልል ደቡባዊ ክፍል፣ የጉጂና ቦረና ዞኖች፣ የሲዳማ ክልል እንዲሁም የደቡብና ደቡብ ምዕራብ አካባቢዎች እስከ 55 በመቶ የሚሆነውን የዝናብ መጠን የሚያገኙበት ዋነኛ ወቅታቸው እንደሆነ ተጠቁሟል።

‎የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አሳምነው ተሾመ እንደተናገሩት ፣ የደቡብና ምስራቅ ትግራይ፣ የምስራቅ አማራ፣ የምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች፣ አዲስ አበባና የመካከለኛው ኢትዮጵያ ክፍሎች ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በመሆኑ ከቀላል እስከ ከባድ ዝናብ ይጠበቅባቸዋል።

‎የሚጠበቀው የዝናብ መጠን የእርሻ ስራዎችንና የአካባቢ ጥበቃ ተግባራትን ለመከወን እጅግ አመቺና ተስማሚ በመሆኑ ምንም ዓይነት ጉዳት እንደማያስከትል ታውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...