የካራማራ ድል የኢትዮጵያዊያንን የማይበገር አንድነት፣ ፅናትና የጀግንነት ወኔ ለዓለም ያስመሰከረበት ደማቅ የታሪክ ገጽ መሆኑን የቀድሞው የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎችና ፖሊስ ሠራዊት ማህበራት ህብረት ገለፀ።
የካቲት 26 ቀን 2018 ዓ.ም የሚከበረውን 48ኛውን የካራማራ ድል በዓል በማስመልከት በመከላከያ መኮንኖች ክበብ በተካሄደው የፓናል ውይይት ላይ ካራማራ የኢትዮጵያ ልጆች ታሪካዊ ጠላቶቻቸውን በጋራ በመመከት ድል የተቀዳጁበት በመሆኑ “የዘመኑ ዓድዋ” መባል እንደሚገባው ተገልጿል ።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የቀድሞ የህብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ወደር የሌለው ጀግና ሜዳይ ተሸላሚ ብርጋዲየር ጄነራል ተስፋዬ ሀብተ ማርያም፣ የቀድሞ የ18ኛው ተራራ ክፍለጦር አዛዥ ሜጄር ጄነራል መርዳሳ ሌሊሳን ጨምሮ ከባህር፣ ከአየርና ከምድር ጦር የተውጣጡ አንጋፋ የጦር መሪዎች ድሉ የኢትዮጵያዊያን አንድነት ህያው ምስክር መሆኑን አስታውሰዋል።
የፓናል ውይይቱን የመሩት ሻለቃ ዋለልኝ ከበደ በወቅቱ የዚያድባሬ ወራሪ ጦር ዘመናዊ ትጥቅ ታጥቆ ቢመጣም፣ የኢትዮጵያ ሠራዊት ግን በሀገራዊ ፍቅርና በጀግንነት ወኔ ድል ማድረጉን ገልጸው፤ ይህም ቴክኖሎጂ ባልዘመነበት ዘመን በሀገራዊ ወኔ የዘመነውን ወራሪ አሸንፎ ሀገር ለማስረከብ የተከፈለ መስዋዕትነት መሆኑን አስገንዝበዋል።
ካራማራ የኢትዮጵያዊያን አንድነት ህያው ምስክር
Date:
