ኢራን ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በፈጸመችው የአጸፋ ጥቃት 220 የአሜሪካ ወታደሮችና አዛዦች መገደላቸውንና መቁሰላቸውን አስታወቀች።
ፕሬስ ቲቪ እንደዘገበው የኢራን “ኻታም አል-አንቢያ” ማዕከላዊ ቃርያ ቃል አቀባይ ሌተና ኮሎኔል ኢብራሂም ዞልፋጋሪ እንደገለጹት፣ በባህሬን በሚገኘው የአሜሪካ አምስተኛ የባህር ኃይል ክፍለ ጦር ላይ በተፈጸመ ጥቃት 21 ወታደሮች ተገድለዋል።
በተጨማሪም በአል-ዳፍራ አየር ማረፊያ በሚገኘው የአሜሪካ ወታደራዊ ካምፕ ላይ በደረሰ ጥቃት ወደ 200 የሚጠጉ ወታደሮች መገደላቸውንና መቁሰላቸውን ኢራን ገልጻለች።
በፋርስ ባሕረ ሰላጤ ሰሜናዊ ክፍልም የአሜሪካ ንብረት የሆነ የነዳጅ ጫኝ መርከብ ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተጠቅሷል።
ይሁን እንጂ አሜሪካም ሆነ ገለልተኛ ወገኖች እስካሁን ይህንን መረጃ አላረጋገጡም።
