አውስትራሊያ ለኢራናውያኑ ተጫዋቾች የሰብዓዊ ቪዛ ፈቀደች

Date:

በአውስትራሊያ አስተናጋጅነት በተካሄደው የእስያ ዋንጫ ላይ ተሳታፊ የነበሩ አምስት የኢራን ሴት ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች የአውስትራሊያን የሰብዓዊ ቪዛ ማግኘታቸው ተረጋግጧል።

ተጫዋቾቹ ይህንን ዕድል ያገኙት ባለፈው ሳምንት ከደቡብ ኮሪያ ጋር በነበራቸው ጨዋታ ላይ የሀገራቸውን ብሔራዊ መዝሙር አንዘምርም በማለታቸውና በኢራን መንግሥት ሊደርስባቸው የሚችለውን አደጋ በመፍራት ነው።

ይህ ድርጊት በቴህራን ባለሥልጣናት ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን፣ ድርጊቱን “በጦርነት ወቅት የተፈጸመ ክህደት” በማለት ከባድ ቅጣት እንዲጣልባቸው ጥሪ ቀርቦ ነበር።

የአውስትራሊያ የአገር ውስጥ ጉዳይ
ሚኒስትር ቶኒ ቡርኬ እንደገለጹት፣ ተጫዋቾቹ በአሁኑ ወቅት ደህንነቱ በተጠበቀ ስፍራ ይገኛሉ።

ሚኒስትሩ አክለውም ተጫዋቾቹ ራሳቸውን እንደ ፖለቲካ አክቲቪስት ሳይሆን እንደ ስፖርተኛ ብቻ እንደሚመለከቱ ቢገልጹም፣ ለደህንነታቸው ሲባል ጥበቃ እንደተደረገላቸው አስታውቀዋል።

ቀሪዎቹ የቡድኑ አባላትም ተመሳሳይ ጥያቄ እንዲያቀርቡ ግብዣ ቢደረግላቸውም፣ አምስቱ ተጫዋቾች ግን በውሳኔያቸው ጸንተው አውስትራሊያ ለመቆየት መርጠዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ካናዳ ምዝገባም ሆነ ስምሪት አልተጀመረም

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መቀመጫውን ካናዳ ካደረገው "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል"...

የክቡር ዶክተር ጋሽ መሐሙድ አዲስ አልበም ለአድማጮች ሊደርስ ነዉ

ታዋቂው ድምፃዊ ክቡር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አሕመድ «ለታሪክ» የተሰኘውንና...

ሜታ ‘ፌስቡክ እና ኢንስታግራም በቀረበባቸው ክስ 18 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ

ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ሜታ በፌስቡክ እና በኢንስታግራም ምክንያት...