ኢባትሎ የሀገሪቱን የትራንስፖርት አቅም የሚያሳድጉ 100 አዳዲስ ተሽከርካሪዎችን ስራ አስጀመረ

Date:

​የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ (ኢባትሎ) የሀገሪቱን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አቅም ይበልጥ ለማሳደግና ቀልጣፋ አገልግሎትን ለማረጋገጥ ግዙፍ ኢንቨስትመንት ያረፈባቸውን 100 አዳዲስ ተሽከርካሪዎች በዛሬው ዕለት በይፋ ስራ አስጀምሯል።

የኢባትሎ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አብዱልበር ሸምሱ በወቅቱ እንደተናገሩት፣ እነዚህ ተሽከርካሪዎች ድርጅቱ ካሉት 556 ተሽከርካሪዎች ጋር ተዳምረው የጭነት ፍሰቱን ለማሳለጥና የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለመደገፍ ትልቅ ሚና ይኖራቸዋል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ የክብር እንግዳ ሆነው የተገኙት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) በበኩላቸው እንደገለፁት፤ አሽከርካሪዎቹ የኢትዮጵያን ስም በድንበር ተሻጋሪ መንገዶች ላይ ከፍ ያደረጉ የኢኮኖሚ ጀግኖች መሆናቸውን በመጥቀስ፣ በሀገር ፍቅርና በሙያ ስነ-ምግባር ተግተው ስራቸውን እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።

በመርሃ-ግብሩ ማጠቃለያ ላይ ተሽከርካሪዎቹን ለአገልግሎት ብቁ በማድረግ ረገድ በቴክኒክና በጥገና ስራ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ የድርጅቱ ሰራተኞች የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...