“መቄዶንያ ተስፋ ለቆረጡት ተስፋን የመለሰ ማዕከል ነው” ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀሥላሴ

Date:

  የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀሥላሴ እና ባለቤታቸው በመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን ማዕከል በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል።

መቄዶንያ አረጋውያኑን ለመርዳት የጀመረውን የገቢ አሠባሠብ መርሐግብርም አስጀምረዋል።

ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ “መቄዶንያ የርህራሄ እና ተስፋ ለቁረጡት ተስፋን እየመለሰ የሚገኝ ማዕከል ነው” ብለዋል።

መንግሥት ለአረጋውያኑ ከሚያደርገው የመቋቋሚያ ድጋፍ መርሐግብር በተጨማሪ ግለሰቦች እና ድርጅቶች አረጋውያንን መርዳታቸው ወገናዊ ኀላፊነትን መወጣት ነው ብለዋል።

የመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን ማዕከል  ከ9ሺህ በላይ አረጋውያንን እና የአዕምሮ ህሙማንን እያገዘ ይገኛል።

መቄዶንያ በኢትዮጵያ በ56 ከተሞች ማዕከል የከፈተ ሲኾን በ14 ከተሞች ሕንጻ እየገነባም ይገኛል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...