ከ5 ሺህ 800 በላይ ፍቺዎች በአዲስ አበባ በስድስት ወራት ውስጥ  ተመዝግበዋል

Date:

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በስድስት ወራት ውስጥ 19 ሺሕ 800 ጋብቻዎች እና 5 ሺሕ 805 ፍቺዎች መመዝገባቸውን የከተማዋ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታውቋል።

የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጥጋቡ ሹመይ እንዳሉት ለተለያዩ ማኅበራዊ አገልግሎቶች የፍቺ ማስረጃ እንደ ቅድመ ሁኔታ መጠየቁ የዘገዩ ፍቺዎች እንዲመዘገቡ አስችሏል፡፡

በዚህም ከተመዘገቡት ፍቺዎች መካከል 1 ሺሕ 750 ያህሉ ፍቺ በተፈጸመ በ30 ቀናት ውስጥ የተመዘገቡ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ 695ቱ ደግሞ ዘግይተው የተመዘገቡ መሆናቸውን የዘገበው ኤ ኤም ኤን ነው ።

ይህም የምዝገባ ቁጥር ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከሁለት ሺህ በላይ ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...

በምክክሩ ሕዝበ ውሳኔ የተጠየቀባቸው ጉዳዮች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 15ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች በተጠናቀሩ...

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...