|በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ትልቅ አሻራ ካኖሩት አንጋፋው አሸናፊ ግርማ እና ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ዓለም አቀፍ ድልድይ በመሆን ከሚታወቁት ዮሐንስ ዘውዱ (ጆኒ ቪጋስ) ጋር በመሆን ለታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ቁሳቁሶችን የማሰራጨት ተግባር ትናንት በ 35 ሜዳ መስቀል ፍላወር አከባቢ ተከናውኗል።
የዕለቱ መርሃ ግብር ለወጣቶች ቁሳቁስ ከመስጠት ባለፈ፣ በውስጣቸው ያለውን ተስፋ የማደስ፣ ህልማቸውን እንዲያሳድጉ የማነቃቃት እና የወደፊት ሕይወታቸው አሁን ካሉበት ሁኔታ በላይ መሆኑን የማሳሰብ ዓላማ ያለው ነው።
እንደ አሸናፊ ግርማ እና ዮሐንስ ዘውዱ ያሉ መሪዎች ለቀጣዩ ትውልድ አዳዲስ በሮችን በመክፈትና ዕድሎችን በመፍጠር ረገድ የሚያደርጉት ጥረት የሚደነቅ ነው።
ወጣቶችን ማብቃት ማለት ሀገርን ማብቃት ነው። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሩህ ተስፋ የሚጀምረው ዛሬ በእነዚህ ታዳጊዎች ላይ ከሚዘራው እምነትና ድጋፍ ነው።
ወጣቶች ማንኛውም ነገር እንደሚቻል እንዲያምኑ ማድረግ የሁላችንም ኃላፊነት ነው።
