ዩናይትድ ኪንግደም አሜሪካ የጦር ሰፈሯን እንድትጠቀም መፍቀዷ ተገልጿል። ይህን ተከትሎም ኢራን የብሪታንያ ዜጎችን አስጠቅቃለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር “አሜሪካ በሆርሙዝ ሰርጥ የኢራን ሚሳዔል ማምረቻዎችን ለማውደም በምታደርገው ጥረት ዩናይትድ ኪንግደም እገዛ ታደርጋለች” ብለዋል።
ካሁን ቀደም የትራምፕን ጥያቄ ውድቅ ያደረጉት ስታርመር፣ “አሜሪካ የእኛን የጦር ሰፈር መጠቀም ትችላለች” ነው ያሉት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር አቋማቸውን የቀየሩት ኢራን በገልፍ ሀገራት በሚገኙ የዩናይትድ ኪንግደም የጦር ሰፈር ላይ ጥቃት በማድረሷ መሆኑ ተገልጿል።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ደግሞ፣ “ኢራን ራሷን ለመከላከል ያላትን መብት ትጠቀማለች” ብለዋል።
“አብዛኛው የብሪታንያ ህዝብ የአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት አካል መሆን እንደማይፈልግ እናውቃለን” በማለት ገልጸዋል።
“ስታርመር የራሱን ህዝብ ለመበደል የሀገሩን የጦር ሰፈር ለወራሪ ፈቅዷል” ያሉት ሚኒስትሩ፣ “የብሪታንያ ዜጎች ደህንነት አደጋ ውስጥ ይገባል” ሲሉም ገልጸዋል።
