ኖ ሞር’ ቴአትር በአሜሪካ ለታዳሚ ሊቀርብ ነው

Date:

በአገር ውስጥ መድረኮች በነበረው ቆይታ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው ‘ኖ ሞር’ (No More) የተሰኘው ቴአትር፣ የባህር ማዶ ጉዞውን በመጀመር በአሜሪካ ዴንቨር ኮሎራዶ ለታዳሚ ሊቀርብ ነው።

ተውኔቱ “በደል የፈፀሙ ሰዎች ተገቢውን ምላሽ ሊያገኙ ይገባል” የሚል ጠንካራ ማህበራዊ መልዕክትን በአስቂኝ ዘውግ አዋህዶ የያዘ ስራ ነው።

ቴአትሩ በኢትዮጵያ ለእይታ በበቃበት ወቅት አራት ተዋንያንን እና ሦስት የቴክኒክ ባለሙያዎችን በማሳተፍ ጥራት ያለው ዝግጅት ማቅረቡ ይታወሳል።

ለኮሎራዶው ዝግጅት በተደረገው ማሻሻያ መሰረት ቴአትሩ የመጀመሪያ ተዋንያን ላይ መጠነኛ ለውጥ ተደርጓል።

‘ኖ ሞር’ በሰው ልጅ ግንኙነት ውስጥ የሚፈጠሩ በደሎችንና ለበደሎቹ የሚሰጡ ምላሾችን በትውፊትና በዘመናዊ የቴአትር አቀራረብ የሚተነትን ነው።

ስራው በዴንቨርና አካባቢው ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የጥበብ ጥምን ለማርካት ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን፥ በቅርቡም የመድረክ ቀኑና የትኬት ሽያጭ ዝርዝር ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል።

ይህ ዝግጅት የኢትዮጵያ ቴአትር ከሀገር ውስጥ አልፎ በዓለም አቀፍ መድረኮች ያለውን ተቀባይነት ለማሳደግ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኢትዮጵያዊዉ የመጀመሪያው የአይን ሐኪም ዶክተር ጳውሎስ አረፉ

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የዓይን ሐኪም እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓይን...

ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች በዓለም አቀፍ የሮቦቲክስ ውድድር 3ኛ ወጡ

በካናዳ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የሮቦቲክስ ውድድር ላይ የተሳተፉት የኢትዮ...

ሁቲዎች የሳዑዲ የነዳጅ ማጣሪያ ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ገለጹ

የኢራን አጋር የሆኑት ሁቲዎች የሳዑዲ አራምኮ ጃዛን ነዳጅ ማጣሪያን...

በዓለም ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 2ኛ የወርቅ ሜዳሊያ አገኝች

በሴቶች 3 ሺህ ሜትር የተወዳደሩት  ዮርዳኖስ ጽጋብ እና ሽቶ...