እሁድ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ

Date:

መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደረገው ዓለም አቀፉ የዛይድ የበጎ አድራጎት የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ዱባይ፣ ኒውዮርክ፣ ቤይጂንግ እና ናይሮቢ ሲካሄድ ቆይቶ ነገ ዕሁድ ሚያዝያ 25 ቀን 2018 ዓ/ም በአዲስ አበባ ይከናወናል።

ሩጫው ከመስቀል አደባባይ መነሻውን አድርጎ በለገሀር መብራት፣ በብሔራዊ ቴአትር መብራት አድርጎ የቀድሞው EBC መብራት ላይ ዞሮ በሠንጋ ተራ መብራት፣ በሜክሲኮ አደባባይ፣ በቡናና ሻይ ለገሀር በማድረግ ፍጻሜው መስቀል አደባባይ ይሆናል።

ይህ የጎዳና ላይ ሩጫ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅም የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ።

በዚህም መሠረት፦

👉 ከቅዱስ ዑራኤል ወደ መስቀል አደባባይ (ባምቢስ ወይም መቅረዝ ሆስፒታል ላይ)

👉 ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ)

👉 ከጥላሁን አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ጥላሁን አደባባይ ላይ )

👉 ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ (ለገሀር መብራት ላይ)

👉 ከለገሀር ቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድየም (ለገሀር ቴሌ ማቋረጫ ላይ)

👉 ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ (ሀራምቤ መብራት ላይ)

👉 ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ (ብሔራዊ ቤተ መንግስት መስቀለኛ ላይ) ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ የሩጫ ፕሮግራሙ እስኪጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ዝግ ይሆናሉ።

በተጨማሪ ለዚሁ ፕሮግራም ሲባል ከዛሬ ሚያዝያ 24 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በመስመሮቹ ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...