ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው ንጉሥ ተብሎ ለሚጠራው ለክቡር ዶክተር ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ የሚሆን ግርማ ሞገስ ያለው ሐውልት 6 ኪሎ አምበሳ ግቢ አጠገብ ተሠርቶ ሚያዝያ 27 2018 ዓ.ም በይፋ ተመርቋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ለታላቁ የጥበብ ሰው ያለውን አክብሮት ለመግለጽ ያስገነባው ይህ ሐውልት፣ በስድስት ኪሎ አካባቢ ወደ ምኒልክና ፈረንሳይ በሚወስደው መንገድ መገናኛ ላይ ቆሟል።
ጥላሁን ገሠሠ ስለ ሀገር፣ ስለ ፍቅር፣ ስለ እናትና ስለ ጀግንነት ያልዘፈነበት ርዕስ የለም። በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞና በሱዳንኛ ዜማዎቹ ህዝብን ሲያቆራኝ የኖረ ባለውለታ ነው።
ሚያዝያ 11 ቀን 2001 ዓ.ም. በ68 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ቢለየንም፣ ዜማዎቹ ግን ከትውልድ ትውልድ ተሻግረው ዛሬም የነፍሳችን ምግብ ናቸው።
የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ
Date:
