ከሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ጋር በተያያዘ እርስዎ በአካል ወደ ባንካችን ቅርንጫፎች ሳይመጡ በስልክ ተደውሎ የሚሰጥ ምንም አይነት አገልግሎትም ሆነ የአሠራር ሂደት የሌለን መሆኑን እያሳወቅን፤ የይለፍ ቃልዎን ለሌላ ሶስተኛ ወገን ተጋላጭ ባለማድረግ በጥንቃቄ እንዲገለገሉ እናሳውቃለን፡፡
እንዲሁም “ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው” በሚል በስልክ በሚላክ መጠይቅ ምንም አይነት መረጃዎን እንደማንጠይቅዎ በመረዳት እራስዎን ከአጭበርባሪዎች እንዲጠብቁ እናሳስባለን፡፡
በተጨማሪም ፦
*ከባንክ ነው በሚል የሚደርስዎትን የስልክ ጥሪ ትክክለኛነት ወደ ባንካችን ቅርንጫፍ በመሄድ ወይም ወደ 951 በመደወል ሳያረጋግጡ ምንም ዓይነት እርምጃ አይውሰዱ፣
*የአፕሊኬሽንም ሆነ USSD ተጠቃሚ ከሆኑ የይለፍ ቃልዎን ከአራት እስከ አስር ዲጂት(ቁጥሮች) ይጠቀሙ፤
*የሞባይል መተግበሪያዎችን (Applications) ወይም ማስፈንጠሪያዎችን (Links) ከማይታወቅና ትክክለኛ ካልሆኑ ምንጮች ስልክዎ ላይ አይጫኑ፤
*ማንኛውንም አይነት መተግበሪያ ከ-Playstore እና ከAppstore ብቻ አውርደው ይጠቀሙ፤
*የዲጂታል የባንክ አገልግሎት የሚስጥር ቁጥርዎን ለማንም አያሳውቁ፤ ሞባይል ስልክዎ ላይ ወይም ማንኛውም ነገር ላይ አይፃፉ፣ ጠንካራ የሚስጥር ቁጥር ይጠቀሙ፣
*ጓደኛ ወይም ዘመድ በመምሰል በማንኛውም አይነት የማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም የገንዘብ ዝውውር/ብድር ሲጠየቁ ክፍያውን ከመፈፀምዎ በፊት መልዕክቱ ከትክክለኛ ወገን የተላከልዎት መሆኑን ያረጋግጡ፤
*በተለያዩ ስልቶች ከሚፈፀሙ ስርቆቶችና ማጭበርበሮች እራስዎን ይጠብቁ፤
*የአሻራ ደህንነት ማጠናከሪያን ይጠቀሙ፤
*መረጃ ለማግኘት የባንካችንን ቅርንጫፎች፣ ወደ 951 በመደወል እና ትክክለኛ የባንካችንን የማህበራዊ ትስስር ገፆች ይጠቀሙ፡፡
*የ*889# ብቻ ተጠቃሚ ከሆኑ እባክዎ ለደህንነትዎ ይበልጥ አስተማማኝና ቀልጣፋ እንዲሁም ተጨማሪ አገልግሎት ወደሚያስገኝልዎ የሞባይል መተግበሪያ ይዛወሩ፡፡
*
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!!
