ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት የህጻናት መጽሐፍት ደራሲ እና የልጆች ፕሮግራም አዘጋጅ ኮሜድያን አስረስ በቀለ (ቼሪ) “ኮሚኩ ሙዝ” የተሰኘውን አዲስ የልጆች መጽሐፍ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት በማስመረቅ ለንባብ አብቅቷል።
አስረስ በቀለ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የልጆች ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት የሚታወቅ ሲሆን፣ “ቼሪ” የተሰኘውን የልጆች ካራክተር በመፍጠር በህጻናት መዝናኛና ትምህርት ዘርፍ ጉልህ አስተዋፅኦ አበርክቷል።
ደራሲው ከ15 በላይ የልጆች ተረት መጻሕፍትን የጻፈ ሲሆን፣ በ2022 እ.ኤ.አ በEthiopia Reads Children’s Reading Summit ላይ ለህጻናት ሥነ-ጽሑፍ ባበረከተው አስተዋፅኦ እውቅና አግኝቷል።
