በመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሥር በሚተዳደሩ የጨልጨል እና የወልመል መስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ 3.69 ቢሊዮን ብር ያለ አግባብ መባከኑን ተነገረ።
ከ2011 እስከ እስከ 2017 ዓ.ም የነበረውን አፈጻጸም የገመገመዉ የፌደራል ዋና ኦዲተር ፤ ፕሮጀክቶቹ ያለበቂ ምክንያት የውል ማሻሻያ እንደተደረገባቸውና ከኮንትራት ውጪ በጀት እንደፈሰሰባቸው አረጋግጧል።
በተለይም በቸልቸል ፕሮጀክት ለቅንጦት ተሽከርካሪዎች ብቻ ከ132 ሚሊዮን ብር በላይ መመደቡና የሐሰት የክፍያ ሰነዶችን በመጠቀም ለተቋራጮች ተጨማሪ ክፍያ መፈጸሙ ተጋልጧል።
በቅድመ-ዕቅድ እጦት እና በደካማ ቁጥጥር ምክንያት ፕሮጀክቶቹ ከ38 ወራት በላይ ዘግይተዋል።
capital
