የኢራኑ ከፍተኛ መሪ ሞጅተባ ኻመነኢ እሁድ ዕለት በቴሌግራም ገጻቸው ባሳፈሩት መልዕክት፣ እስላማዊቷ ሪፐብሊክ ሄዝቦላን መደገፏን እንደ ዋና ስትራቴጂካዊ ፖሊሲ እንደምትቀጥልበት ጠቁመው፤ «ከጂሃድና ከእምቢተኝነት ውጭ ሌላ ምንም አይነት መንገድ የለም» ሲሉ ገልጸዋል።
መሪው አክለውም፤ በእምቢተኝነት ጎዳና ላይ ጸንቶ መቆም «መለኮታዊ ድልን» እንደሚያስገኝ በመጠቆም፣ የሄዝቦላን አቋም «አነቃቂ መልእክት» ሲሉ አሞግሰውታል።
በተጨማሪም የሊባኖስን ግዛታዊ አንድነት ማስጠበቅና የእስራኤል ጥቃቶች «ሙሉ በሙሉና ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ» እንዲቆሙ ማድረግ፣ ከአሜሪካ ጋር ጦርነቱን ለማቆም የሚደረገው ስምምነት የመጀመሪያዎቹ ቅድመ ሁኔታዎች መሆናቸውን ኻመነኢ አብራርተዋል።
