ኢራን ከአሜሪካ ጋር በሚደረገው ድርድር ሙሉ በሙሉ እንዳልወጣች፣ ነገር ግን ለጊዜው አቁማ እንደነበር አስታወቀች ።
በኳታር እና ፓኪስታን አዘጋጅነት የቀረበውን የሰላም ውይይት እንደገና የማስጀመር የውሳኔ ሃሳብ በተመለከተ ዋሽንግተን እና ቴህራን ምላሾቻቸውን አቅርበዋል ተብሏል።
ይህ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ የመጣው ለሁለት ሳምንታት ያህል ከተካሄደው የአየር ድብደባ በኋላ ለሁለት ተከታታይ ምሽቶች ምንም ዓይነት የአሜሪካ ጥቃት አለመፈጸሙን ተከትሎ ነው።
ቴህራን ድርድሩ ከአሜሪካ ጋር በተደረሰው የስምምነት ማዕቀፍ መሠረት በጄኔቫ፣ ዶሃ ወይም ኢስላማባድ ውይይቱን ለመቀጠል ፍላጎት እንዳላት ገልጻለች።
የአሜሪካ ጥቃት መገታቱን ተከተሎ የኢራን ኃይሎችም አጸፋዊ ጥቃታቸውን ማቆማቸውን አስታውቀዋል።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ጦር ለወታደራዊ እርምጃ ዝግጁ እንደሆነ ቢገልጹም፣ ለዲፕሎማሲያዊ ንግግሮች ዕድል ለመስጠት ሲባል ጥቃቱ እንዲቆም ማድረጋቸውን ተናግረዋል።
