ኢትዮጵያ ቡና በ8 ቢልዮን ብር ስታድየም ሊገነባ ነዉ

Date:


አዲሱ የክለቡ ፕሬዝዳንት እስራኤል ደገፋ (ዶ/ር) ክለብ አሰልጣኝ ገብረ መድህን ኃይሌን ባስፈረመበት ይፋዊ መግለጫ ላይ የተለያዩ ጉዳዮችን አንስተዋል።

ኢትዮጵያ ቡና በዘላቂነት ላይ ትኩረቱን አድርጎ እንደሚሰራ የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ “ተረጂ ሳይሆን ረጂ” መሆን እንዲችሉ እየሰሩ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

“ቤቴን ለመረከብ የቤት ስራዬን ስሰራ ቆይቻለው።” ያሉት ዶ/ር እስራኤል ከሚድያ ጋር ያልተገናኙትም በዚሁ ምክንያት መሆኑን ጠቁመዋል።

“የስቴድየም የዲዛየን ስራ ጨርሰናል። 8 ቢልየን ይፈጃል። በቀጣይ እሱን የማስጀመር ስራውን እንሰራለን።” ሲሉም ክለቡ የስታድየም ባለቤት ለመሆን ያለውን እቅድ ገልፀዋል።

“ኢትዮጵያ ቡና እንደምትሉት ደሃ አይደለም።” ያሉት ፕሬዝዳንቱ “ከሌሎች ክለቦች የተሻለ ሃብትም ፣ መገልገያም አለን።” ሲሉ ገልፀዋል።

ከአሰልጣኝ ገብረ መድህን ኃይሌ ጋር ያሰሩት ውል የ2 አመታት የመሆኑ ምክንየትም ከፋይናንስ ጋር እንደማይያያዝ አሳውቀዋል።

ከደሞዝ እና ጥቅማ ጥቅም ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰው ከእውነት የራቀ መሆኑ ሲጠቆም ፣ የገንዘቡ መጠን ምን ያህል ነው የሚለው ጉዳይ በሁለት ተዋዋይ ወገኖች መሃል ስምምነት ሳይኖር ምላሽ እንደማይሰጥበት ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጄኤፍኤም 106.7 የሬዲዮ ጣቢያ ለ6 ወራት ታገደ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባደረገው የይዘት ክትትልና የኢንስፔክሽን ምልከታ...

ሱልጣን ቢን ኻሊፋ ግሩፕ በኢትዮጵያ በሆቴል ዘርፍ ሊሰማራ ነው

በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር...

የአሜሪካ የታክስ ህግ የስፔንን የዓለም ዋንጫ ሽልማት ስጋት ላይ ጣለ

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከዓለም ዋንጫ ሊያገኘው ከሚችለው 50 ሚሊዮን...

ህወሓት ከሌሎች ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር የሚደረግ ጥምረት አስፈላጊ መሆኑን ገለጸ

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ...