የአሜሪካ ጦር ለሰባት ተከታታይ ምሽት በኢራን ላይ ድብደባ መፈጸሙን አስታወቀ

Date:

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቴህራን ጋር የተደረሰው የተኩስ አቁም “ማብቃቱን” ካስታወቁ በኋላ የአሜሪካ ጦር ለሰባተኛ ምሽት ድብደባ መፈጸሙን አስታወቀ።

የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንትኮም) በኤክስ ገጹ ላይ ባጋራው መግለጫ፣ ጦሩ “የቅኝት ጣቢያዎችን፣ የወታደራዊ ሎጂስቲክ መሠረተ ልማቶችን፣ ከምድር በታች የሚገኙ የጦር መሣሪያ ማከማቻዎችን እና የባሕር ኃይል አቅሟ” ላይ ድብደባ መፈጸሙን አስታውቋል።

የኢራን አብዮታዊ ዘብ በበኩሉ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ በተቀበሩ ፈንጂዎች ሁለት የነዳጅ ጫኝ መርከቦች መፈንዳታቸውን ገልጿል። ሴንትኮም ግን መረጃው ሐሰት ነው ሲል አስተባብሏል።

የዮርዳኖስ ጦር ምሽቱን ከኢራን የተወነጨፉ አስር ሚሳዔሎችን ማክሸፉን እና ምንም ዓይነት ጉዳት አለማድረሳቸውን ገልጿል።

ሴንትኮም ለበርካታ ሰዓታት ድብደባውን ከፈጸመ በኋላ ከእኩለ ለሌሊት በፊት ማቆሙን በመግለጫው ላይ አመልክቷል።

ማዕከላዊ ዕዙ በመግለጫው ሌሊቱን ለፈጸማቸው ድብደባዎች “የአሜሪካ ጦር ተዋጊ ጄቶችን፣ ድሮኖችን እና የባሕር ኃይሉን ተጠቅሟል” ብሏል።

ፋርስ የዜና ወኪል በበኩሉ ሁለት የነዳጅ ጫኝ መርከቦች “ፈንጂ በተቀበረበት የሆርሙዝ ወሽመጥ ደቡባዊ ክፍል ሲያልፉ ፈንድተው በእሳት ተያይዘዋል” ብሎ የዘገበ ሲሆን ሴንትኮም በኤክስ ገጹ ላይ “ልክ እንደ ሌሎቹ የአብዮታዊ ዘቡ መረጃዎች ሁሉ ይህም ሐሰት ነው” ሲል አስተባብሏል።

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል እየተካሄደ ባለው ውጊያ የተነሳ በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚያልፉ መርከቦች ቁጥር እጅጉን ቀንሷል።

የሆርሙዝ ወሽመጥ የዓለም አንድ አምስተኛ የነዳጅ ዘይት እና የተፈጥሮ ጋዝ የሚተላለፍበት መስመር ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጄኤፍኤም 106.7 የሬዲዮ ጣቢያ ለ6 ወራት ታገደ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባደረገው የይዘት ክትትልና የኢንስፔክሽን ምልከታ...

ሱልጣን ቢን ኻሊፋ ግሩፕ በኢትዮጵያ በሆቴል ዘርፍ ሊሰማራ ነው

በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር...

የአሜሪካ የታክስ ህግ የስፔንን የዓለም ዋንጫ ሽልማት ስጋት ላይ ጣለ

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከዓለም ዋንጫ ሊያገኘው ከሚችለው 50 ሚሊዮን...

ህወሓት ከሌሎች ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር የሚደረግ ጥምረት አስፈላጊ መሆኑን ገለጸ

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ...