እስራኤል በኢራን ላይ በሚደረገው ጦርነት አትሳተፍም

Date:

የቀኝ-ዘመም አቋም ያላቸው የእስራኤል የፋይናንስ ሚኒስትር ቤዛሌል ስሞትሪች ይህንን አስተያየት የሰጡት በማዕከላዊ እስራኤል በምትገኘው ያድ ቢንያሚን በተደረገ ጉባኤ ላይ ነው።

የእስራኤል መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት፣ “በአሁኑ ወቅት የእስራኤል መንግስት በዚህ የጦርነት ዘመቻ ለመሳተፍ ምንም ዓይነት ፍላጎት የለውም” ብለዋል።

“አሁን ያለው ሁኔታ ለእኛ ምቹ ነው፤ ስለዚህ ራሳችንን ወደዚህ ሁኔታ ለመክተት ምንም ፍላጎት የለንም። ለማንኛውም ሁኔታ ግን ዝግጁ ነን።” ሲሉ አክለዋል፡፡

በቀጠለዉ የኢራን እና የአሜሪካ የተኩስ ልዉዉጥ የኢራኑ እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ኃይልበባህሬን ውስጥ በሚገኝ አንድ የአሜሪካ የንግድ ተቋም ላይ ጥቃት ማድረሱን አስታዉቋል።

ከፊል-መንግስታዊ የሆነዉ የታስኒም የዜና ወኪል ባሰራጨው መግለጫ መሰረት፣ የዘብ ኃይሉ የአየር እና የጠፈር ኃይል ክሩዝ ሚሳይሎችን በመጠቀም የአማዞን የማዕከላዊ ዳታ መሠረተ ልማት ማውደሙን ገልጿል።

ኃይሉ ይህንን ጥቃት የፈጸመው፣ በቅርቡ አሜሪካ በዳርክሆቪን በሚገኙ የሲቪል መሠረተ ልማቶች ላይ ላደረሰችው ጥቃት የአጸፋ ምላሽ ለመስጠት እንደሆነ አስታውቋል።

በሌላ በኩል የኢራን ጦር በባህሬን የሚገኘውን የአሜሪካ የሼክ ኢሳ ወታደራዊ ጣቢያን በድሮኖች ማጥቃቱን ማስታወቁን የመንግስት የዜና ወኪል ፋርስ ዘገበ።

እንደ ጦሩ ገለጻ፣ ጣቢያው ለአሜሪካ የባህር ኃይል አምስተኛ መርከቦች ቡድን ቁልፍ ከሆኑት ተቋማት አንዱ ሲሆን የአሜሪካን ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ማዕከል ሆኖ ያገለግላል።

ጦሩ አክሎም፣ “ጠላት በኢራን ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት እንዲያቆም እስኪገደድ ድረስ” የማጥቃት እርምጃዎቹ እንደሚቀጥሉ አስታውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጄኤፍኤም 106.7 የሬዲዮ ጣቢያ ለ6 ወራት ታገደ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባደረገው የይዘት ክትትልና የኢንስፔክሽን ምልከታ...

ሱልጣን ቢን ኻሊፋ ግሩፕ በኢትዮጵያ በሆቴል ዘርፍ ሊሰማራ ነው

በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር...

የአሜሪካ የታክስ ህግ የስፔንን የዓለም ዋንጫ ሽልማት ስጋት ላይ ጣለ

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከዓለም ዋንጫ ሊያገኘው ከሚችለው 50 ሚሊዮን...

ህወሓት ከሌሎች ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር የሚደረግ ጥምረት አስፈላጊ መሆኑን ገለጸ

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ...