“በመሃል” ቅዳሜ ይመረቃል

Date:


በእመቤት አብዲሳ የተፃፈው “በመሃል” የተሰኘው የፈጠራ ሥራ የፊታችን ቅዳሜ ነሐሴ 2 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው ኧርባን ሴንተር(የከተማ ማዕከል) ይመረቃል።


በምረቃ መርሀ -ግብሩ ላይ የደራሲዋ እንግዶች፣ ወዳጆች የሚታደሙ ሲሆን የመፅሐፍ ዳሰሳን ጨምሮ ልዩ ልዩ መሰናዶዎችም እንደሚኖሩ ይጠበቃል።


የመፅሐፉ ደራሲ እመቤት አብዲሳ ጅግሳ፣ ከተማሪነት ዕድሜዋ ጀምሮ ለቃላትና ለሃሳብ ፍቅር በማሳደሯ ገና በልጅነቷ ወደ ጽሑፍ ዓለም የገባች ጋዜጠኛ ነች።


የኮሙኒኬሽን ባለሙያ እና አሁን ደግሞ ደራሲ የሆነችው እመቤት በጋዜጠኝነት ሙያዋ በታወቁ ጋዜጦች ላይ በርካታ ማኅበራዊና ባህላዊ አጀንዳዎችን ያነሱ ጽሑፎችን ስታቀርብ ቆይታለች።

የቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ሳለችም የተለያየ ይዘት ያላቸውን ዘገባዎች፣ ቃለ- መጠይቆችና ፕሮግራሞችን በመሥራት ሰፊ ልምድ አካብታለች። በተጨማሪም በኮሙኒኬሽን ባለሙያነት የተለያዩ ማህበረሰባዊና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ በመሥራት ላይ ትገኛለች።


እመቤት ባለፉት ዓመታት ያከማቸቻቸውን የሕይወት ምልከታዎች፣ ስሜቶችና ልምዶች በማጣመር «በመሃል» የተሰኘውን የፈጠራ ሥራዋን ለአንባቢዎች አበርክታለች። በ195 ገጾች የተሰናዳው ይህ መጽሐፍ፣ በስፋት የተቃኙ 14 አጫጭር ታሪኮችን እና 43 ግጥሞችን በውስጡ ይዟል። 450 ብርም እንደሚሸጥ ከደራሲዋ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።


በቅርቡ በ «ንባብ ለሕይወት» ኤግዚቢሽን ላይ ከአንባቢያን ጋር የተዋወቀው «በመሐል» መጽሀፍ የደራሲዋ የፅሑፍ ክህሎት የታየበት ደረጃውን የጠበቀ ሥራ ነው ሲሉ ያነበቡት ሀሣብ ሰንዝረዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ቴህራን ወሽመጡ ወዲያውኑ እንደማይከፈት አስጠነቀቀች

ኦማን ከኢራን ጋር በሆርሙዝ ወሽመጥ ዙሪያ የምታደርገው ንግግር በጥሩ...

ከታክስ በፊት ከ1.54 ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፉን ስኬት ባንክ አስታወቀ

​ስኬት ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 4.1 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ...