በሳይበር ጥቃት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አምስተኛ መሆኗ ተሰማ

Date:

ኢትዮጵያ በሳይበር ተጋላጭነት ከአፍሪካ አገራት 5ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ የኢንተርፖል አዲስ ሪፖርት አመለከተ።

በአህጉሪቱ አጠቃላይ ከታዩ የዲጂታል ጥቃት ተጋላጭነቶች መካከል ኢትዮጵያ 3.3 በመቶ ድርሻ እንዳላት የተገለጸ ሲሆን፣ ፈጣን የቴክኖሎጂ እድገት ጉዞ ከሳይበር ደኅንነት መከላከያ አቅም እና ተቋማዊ ዝግጁነት ቀድመው መሄዳቸው ለዚህ ተጋላጭነት እንደዳረገው ሪፖርቱ አጋልጧል።

በአህጉሪቱ በሳይበር ጥቃት ሳቢያ የሚገጥመው አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ 5 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን የጠቆመው ድርጅቱ፣ አገራትና ድርጅቶች ለሳይበር ደኅንነት የሚያወጡት ወጪ ከ15 ቢሊዮን ዶላር በላይ ማሻቀቡን አመልክቷል።

በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ አገራት ላይ የሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች በሞባይል ገንዘብ ማጭበርበር፣ በቴሌኮሙኒኬሽን መሠረተ ልማቶች እና በወሳኝ ተቋማት ላይ ያተኮሩ መሆናቸው ተመላክቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ቴህራን ወሽመጡ ወዲያውኑ እንደማይከፈት አስጠነቀቀች

ኦማን ከኢራን ጋር በሆርሙዝ ወሽመጥ ዙሪያ የምታደርገው ንግግር በጥሩ...

ከታክስ በፊት ከ1.54 ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፉን ስኬት ባንክ አስታወቀ

​ስኬት ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 4.1 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ...