የተመጣጠነ የምግብ ችግርን ለመቅረፍ አስገዳጅ መመሪያ ተዘጋጀ

Date:

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በንጥረ ነገሮች የበለፀጉ የዘይትና ዱቄት ምርቶችን ለመመዝገብ የሚያስችል አስገዳጅ መመሪያ ማዘጋጀቱን ተከትሎ በመመሪያው ላይ አስተያየት እንዲሰጡበት በሐዋሳ ቅርንጫፍ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በተዘጋጀው መድረክ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቅርንጫፉ የምግብ ተቋማት ህግ ማስፈፃምና ኢንስፔክሽን ዴስክ ኃላፊ አቶ ብሩህ አለማየሁ እንደተናገሩት የተመጣጠነ የምግብ እጥረተ የህብረተሰብ ጤና ችግር መሆኑን ገልፀው መንግስት የህዝብን የአመጋገብ ስርዓት ለማሻሻል የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

እንደአቶ ብሩህ ንግግር ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ምግቦችን በማዕድን፣ ቫይታሚን እና ሌሎች ንጥረ ነገሮች ለማበልፀግ አስገዳጅ መመሪያ ማዘጋጀቱንና ይህ መድረክም ባለድርሻ አካላት በዋነኝነት የዘይትና የዱቄት አምራቾች አስተያየት እንዲሠጡበት የተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡

በመድረኩ በምግብ ማበልፀግ አስፈላጊነት እና የዱቄትና የዘይት አምራች ተቋማት ሊዘረጉት ስለሚገባው የዉስጥ ጥራት ዝርጋታ ፅሁፎች የቀረቡ ሲሆን ባለስልጣኑ ያዘጋጀው አስገዳጅ የምግብ ማበልፀግ መመሪያ ለውይይት ቀርቦ ሠፊ ውይይት ተደርጓል፡፡

በውይይቱ በሐዋሳ ቅርንጫፍ ዱቄትና ዘይት ማምረቻ ፈቃድ ወስደው እየሰሩ ያሉ ተቋማት የተሳተፉ ሲሆን ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችም የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ሐዋሳ ቅርንጫፍና ከዋናው ቢሮ በተገኙ ባለሙያዎች ማብራሪያ ሲሰጥ የቅርንጫፉ  ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ንማኔ እንደተናገሩት የምግብ ማበልፀጉን ተግባራዊ የማያደርጉ ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱ ይቀጥላል ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...