ጠ/ሚ ዐቢይ፡ “መንግስት መቼ ይወድቃል?” ለሚሉ ግምቶች መሠረተ ቢስ ናቸው

Date:

የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ ይወድቃል በሚል የሚናፈሱ ግምቶች መሠረተ ቢስ መሆናቸውንና መንግስታቸው ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ጠንካራ መሠረት ላይ መቆሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ “መንግስት ሰኞ ይወድቃል፣ ማክሰኞ ይወድቃል፣ መስከረም ወይም ጥቅምት ነው መብቂያው” በማለት የሚተነብዩ አካላትን በማስተባበል፣ መንግስታቸው ሥልጣንን ለማስጠበቅ ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱን ብልጽግና መሠረት ለመጣል በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የመንግስትን የዕቅድና የዝግጅት አቅም አስመልክቶ ሲናገሩ፣ ተቃዋሚና አፍራሽ ኃይሎች አንድ እርምጃ ወደፊት ሲያስቡ መንግስት ሃያ እጥፍ አርቆ የሚያስብ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

አያይዘውም ሌሎች ለአንድ ወር ሲዘጋጁ መንግስት ለሃያ ዓመታት የሚያገለግል ዕቅድና ዝግጅት ይዞ እንደሚንቀሳቀስ በመግለጽ፣ መንግስትን ለማፍረስ የሚደረጉ ጥረቶች እንደማይሳኩ አስታውቀዋል።

በመጨረሻም ለሁሉም ወገኖች ጥሪ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የሌሎች ኃይሎች መሣሪያ ከመሆን በመቆጠብ፣ ልዩነቶችን ወደ ጎን በመተውና ለሀገር ግንባታ በጋራ መሥራት የተሻለ አማራጭ መሆኑን አሳስበዋል

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በዩሮፓ ሊግ አምስተኛ ጨዋታ

በዩሮፓ ሊግ አምስተኛ ጨዋታ ጁቬንቱስ ኦሞኑያ ኒኮስያን 4ለ1 በሆነ...

ኢራን አዲስ ጥቃት ቢፈጸምባት መጠነ-ሰፊ የሚሳኤል አጸፋ ልሰነዝር እንደሚችል አስጠነቀቀች

ኢራን በአሜሪካ ወይም በእስራኤል አዲስ ጥቃት የሚፈጸምባት ከሆነ፣ ከዚህ...

የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ዜጎችን በስፖርት ለማሳተፍ የትብብር ውይይት ተካሄደ

የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ዜጎች በስፖርት ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግና...

በአዲስ አበባ የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት በህገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ ቁጥጥር ሊጠናከር ነዉ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋትና የንግድ ስርዓቱን...